ኢራን ከአንድ ዓመት በፊት በ50 አሜሪካዊያን ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል
ማዕቀቡ ከተጣለባቸው ሰዎች መካከል የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠበቃም ይገኙበታል፡፡ኢራን በ15 የአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች፡፡
ኢራን ከሰባት ዓመታት በፊት አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች የምዕራባዊያን ሀገራት ጋር በኑክሌር ማብላላት ዙሪያ ስምምነት ላይ ደርሳ ነበር፡፡
በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን ጊዜ ስምምነት ላይ ደርሳ የነበረችው ኢራን ዶናልድ ትራምፕ ወደ ፕሬዝደንትነት ሲመጡ ይሄንን ስምምነት ውድቅ አድርገው አሜሪካ ለስምምነቱ እንደማትገዛ ማሳወቋ ኢራንን አበሳጭቷል፡፡
የአሁኑ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የ2015ቱ የኢራን ኑክሌር ስምምነት ተግባራዊ በሚሆንበት ጉዳይ ዙሪያ ውይይቶች ኢንዲኖሩ ኢራን ስትወተውት ቆይታለች፡፡
ይሁንና ኢራን የዚህ ታሪካዊ ስምምነት ወደ ቀደመ ይዞታው ሊመለስ አለመቻሉን አስታውቃ ከ15 በላይ የአሜሪካ የአሁን እና የቀድሞ መንግስታት ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጥላለች፡፡
በኢራን ማዕቀብ ከተጣለባው ሰዎች መካከልም በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የስልጣን ዘመን የሀገሪቱ መከላከያ አዛዥ የነበሩት ጆርጅ ቻሲን ጨምሮ የትራምፕ ጠበቃ የነበሩት ሩዲ ጉሊያኒ ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ኢራን በኦስትሪያ መዲና ቬና ላይ ለ11 ተከታተይ ወራት በተካሄደው የኢራን የኑክሌር ስምምነት እንዳይተገበር አስተዋጽኦ አድርገዋል ባለቻቸው ሌሎች ሰዎችም ላይ ማዕቀብ የጣለች ሲሆን
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው በአፍጋኒስታን የአሜሪካንን ጦር ሲመሩ የነበሩት ጀነራል ኦስቲን ስኮት፣ የአሜሪካ ንግድ ዋና ጸሃፊ ዊልበር ሮስ እና ሌሎች ዲፕሎማቶች በኢራን ማዕቀብ ከተጣለባቸው ሰዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
አሜሪካ ኢራን በእስራኤል እና በሌሎች አሻባሪዎች በኢራን ላይ አደጋ እንዲያደርሱ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ናት ስትልም ሀገሪቱ አስታውቃለች፡፡
ኢራን ከአንድ ዓመት በፊት በኢራን አብዮተኛ ጦር ዋና አዛዥ የነበሩት በጀነራል ካሲም ሱሌማኒ ግድያ እጃቸው አለበት በሚል የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንትን ጨምሮ 50 አሜሪካዊያን ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል፡፡