ኢራን በጋዛ ጦርነት ከቀጠለ አሜሪካም የገፈቱ ቀማሽ ትሆናለች ስትል አስጠነቀቀች
ቴህራን የአሜሪካ መሪዎች በፍልስጤም ያለውን የዘር ጭፍጨፋ እየደገፉ ነው ስትል ወቅሳለች
ሀገሪቱ በጋዛ ያለው የዘር ማጥፋት ከቀጠለ አሜሪካ ከእሳቱ አትድንም በማለት ዝታለች
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂን በጋዛ ሰርጥ እስራኤል በፍልስጤም ታጣቂዎች ላይ የምትወስደው አጻፋ ካላበቃ አሜሪካም "ከዚህ እሳት አትተርፍም" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የውጭ ገዳይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት 193 አባላት ባሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በመካከለኛው ምሥራቅ ላይ ባካካሄደው ስብሰባ ነው።
"በፍልስጤም ያለውን የዘር ጭፍጨፋ እያስተዳድሩ ያሉ የአሜሪካ መንግስታት መሪዎች [አሉ] ፤ በቀጣናው ጦርነት መስፋፋትን አንፈልግም። በጋዛ ያለው የዘር ማጥፋት ከቀጠለ ግን ከዚህ እሳት አይድኑም" ሲሉ ተናግረዋል።
እስራኤል ከሦስት ሳምንት በፊት 1 ሽህ 400 ሰዎችን ለገደለው ጥቃት ለመመለስ ጋዛን የሚመራውን ሀማስ ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት ቃል ገብታለች።
እስራኤል ጋዛን በአየር ስትደበደብ የሰነበተች ሲሆ፤ ለመሬት ወረራ እየተዘጋጀች መሆኑን ተናግራለች።
የፍልስጤም ባለስልጣናት በእስራኤል ጥቃት ከሰባት ሽህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል።
ሀማስ ለኢራን ሲቪል ታጋቾችን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፤ በእስራኤል የታሰሩ ስድስት ሽህ ፍልስጤማውያን እንዲፈቱ ዓለም ግፊት መድረግ አለበት ማለቱን አሚራብዶላሂን ተናግርዋል።
"የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ በዚህ በጣም አስፈላጊ ሰብዓዊ ተግባር ከኳታር እና ቱርክ ጋር በመሆን የበኩሉን ሚና ለመጫወት ዝግጁ ነው" ብለዋል።