ኢራን እስራኤል 'ጥቃቷን ካላቆመች' ቀጣናዊ ውጥረቱ እንደሚባባስ አስጠነቀቀች
ቴህራን በቀጣናው ያሉ ሌሎች ወገኖች እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግራለች
ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ "ሀማስን ለማጥፋት" ቃል ገብተዋል
ቴህራን እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ማቆም ካልቻለች ውጥረቱ እንደሚባባስ አስጠንቅቃለች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በክልሉ ያሉ ሌሎች ወገኖች እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሆሴን አሚራብዶላሂን እንደተናገሩት "የጽዮናዊያን ጥቃቶች ካልቆሙ በክልሉ ውስጥ ያሉ የሁሉም እጆች የጥይት ቃታው ላይ ናቸው" ብለዋል።
ባለፈው ሳምንት እስራኤልን በጋዛ ሰርጥ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ፈልጋለች በማለት የከሰሱት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ፤ በጋዛ ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት በመካከለኛው ምስራቅ አዲስ የተቃውሞ ግንባርን ይከፍታል ብለዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ወታደሮቻቸው ወደ ጋዛ ሰርጥ ለመግባት እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት "ሀማስን ለማጥፋት" ቃል ገብተዋል።
የኢራን ከፍተኛ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ በእስራኤል ላይ ታጣቂው የሀማስ ቡድን ባደረሰው ጥቃት ቴህራን ምንም አይነት ተሳትፎ የላትም ብለዋል።
ነገር ግን የእስራኤልን "የማይስተካከል" ወታደራዊ ምላሽ እና የስለላ ሽንፈትን አወድሰዋል።
እስራኤል የኢራን ገዥዎችን ለሀማስ የጦር መሳሪያ በማቅረብ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥረዋል በማለት ስትከስ ቆይታለች።
ቴህራን የጋዛን ሰርጥ ለሚቆጣጠረው ቡድን የሞራል እና የገንዘብ ድጋፍ እንደምትሰጥ ተናግራለች።