ፖለቲካ
ኢራን ፍልስጤም ላይ ለሚፈጸም ወንጀል የአጸፋ ምላሽ እንሰጣለን አለች
ሀገሪቱ ፍልስጤማዊያን ማፈናቀል እና አገልግሎት ማቋረጥ የጦር ወንጀል ነው ብላለች
እስራኤል ለሚሰጠው ምላሽ ኃላፊነት ወሳጅ ናት ተብሏል
ፍልስጤም ላይ የቀጠለው ወንጀል ከተቀናቃኝ ኃይሎች አጸፋዊ ምላሽ ይገጥመዋል ብላለች።
ለመዘዙም ተጠያቂ የምትሆነው እስራኤል መሆኗንም የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተናግረዋል።
እስራኤል ባለፈው ሳምንት አንድ ሽህ 300 የሚሆኑ ሰዎችን ለገደለው የሀማስ ጥቃት ምላሽ ጋዛን በቦንብ እየደበደበች ነው።
እስካሁን በጋዛ የእስራኤል መልሶ ማጥቃት አንድ ሽህ 500 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆሲን አሚራቦዳላሂን ፍልስጤማዊያን ማፈናቀል እና በጋዛ ሰርጥ የውሃና መብራት መስመሮችን ማቋረጥ የጦር ወንጀል ነው ብለዋል።
"አንዳንድ ምዕራባዊያን ባለስልጣናት ለጺዮናዊ ኃይሉ ተቀናቃኝ አዲስ ግንባር ለመፍጠር ያለን ፍላጎት እየጠየቁ ነው። የጦር ወንጀል እየተፈጸመ ባለበት ሁኔታ በሚገባ አለ" ሲሉ ተቀናቃኝ ኃይል እንደሚኖር ተናግረዋል።
"በፍልስጤምና ጋዛ ላይ የቀጠለው የጦር ወንጀል ከሌላው ወገን ምላሽ ይሰጠዋል። ለዚህም ጺዮናዊያንና ደጋፊዎቻቸው ኃላፊነት ይወስዳሉ" ብለዋል።
ሚንስትሩ ተቀናቃኝ ያሏቸውን ወገኖች በስም ባይጠሩም፤ ጥምረቱ ኢራንን፣ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖች፣ ሶሪያ፣ የሊባኖሱ ታጣቂ ሂዝቦላና ሌሎችንም አንጃዎች ያካትታል።