ኢራን እና ቱርክ የኩርድ አማጺያን ከኢራቅ የኩርዲሽ ክልል በመነሳት ጥቃት እያደረሱባቸው እንደሆነ ይከሳሉ
በሰሜን ኢራቅ ውስጥ በሚገኘው የኩርዲስታን ከፊል የራስ ገዝ ግዛት ውስጥ የኢራን ሃይሎች ባደረሱት ድንበር ዘለል የቦምብ ጥቃትሱ 13 ሰዎች ሲገደሉ 58 ሰዎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
የግዛቱ የኩርዲሽ ፀረ ሽብር አገልግሎት (ሲቲኤስ) ባወጣው መግለጫ የኢራን እስላማዊ አብዮት ጠባቂዎች በባሊስቲክ ሚሳኤሎችን እና ወጥመድ የያዙ ድሮኖችን በመጠቀም አራት ዙር የቦንብ ጥቃት አድርሰዋል ብሏል፡፡
የተፈጸመውን የአየር ጥቃት የኢራን መህር የዜና ወኪል የቦምብ ጥቃቱን ማረጋገጡን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የዜና ወኪሉ "በኢራቅ ኩርዲስታን ግዛት በምዕራባዊ ድንበሮች አቅራቢያ የሚንቀሳቀሱትን የአሸባሪ ቡድኖችን ቦታ በድጋሚ ኢላማ አድርጓል" ሲል ዘግቧል፡፡
የኢራን እና የቱርክ ሃይሎች በሰሜን እና በሰሜን ምስራቅ ኢራቅ ውስጥ በኩርዲስታን የሚገኙት የኩርድ ተቃዋሚዎች ከኢራቅ ኩርዲሽ ክልል ካምፖቻቸው በመነሳት በሀገራቸው ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በሚል ክስ በተደጋጋሚ ያጠቃሉ።
የቱርክ መንግስት በሶሪያ ውስጥ በሚገኙ የኩርድ አማጺያንን ለማጥቃት በተለያየ ጊዜ ወታደራዊ ዘመቻ አካሂደዋል፤ በማካሄድም ላይ ይገኛሉ፡፡
በኢራን ተገቢ ያልሆነ አለባበስ ለብሳለች የተባለች ሴት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆና ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ እንደቀጠለ ነው፡፡ ኢራን፤ አሜሪካ በሀገሪቱ የተፈጠረውን አመጽ ኢራንን ለማዳከም እየተጠቀመችበት ነው ስትል ከሳለች፡፡