አየርላንድ ወደ ደሴቷ መጥተው ለሚኖሩ ዜጎች 80 ሺህ ዩሮ እንደምትከፍል ገለጸች
ሀገሪቱ ደሴቲቱ ሰው አልባ እየሆነች መምጣቷን ተከትሎ ነዋሪዎችን ለማበረታታት ሽልማት አዘጋጅታለች
ወደ ደሴቶቹ መሄድ የሚፈልጉ ሰዎች ከሀምሌ አንድ ጀምሮ ማመልከት ይችላሉ ተብሏል
አየርላንድ ወደ ደሴቷ መጥተው ለሚኖሩ ዜጎች 80 ሺህ ዩሮ እንደምትከፍል ገለጸች፡፡
የአውሮፓ ሀገራት የህዝብ ብዛት በየጊዜው እያሽቆለቆለ መምጣቱን ተከትሎ በየጊዜው ዜጎቻቸው ልጆን እንዲወልዱ የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
አሁን ደግሞ አየርላንድ ሰው አልባ ወደ የሆኑ ደሴቶቿን በሰዎች ለመሙላት አዲስ ፖሊሲ ማዘጋጀቷን አስታውቃለች፡፡
አየርላንድ ባዘጋጀችው አዲሱ ደሴቶችን በነዋሪዎች የመሙላት እቅድ መሰረት ዳጎስ ያለ የገንዘብ ሽልማት ያዘጋጀች ሲሆን ወደነዚህ ደሴቶች ለሚያመራ ሰው 80 ሺህ ዩሮ እንደምትሰጥ ተገልጿል፡፡
30 ሰው አልባ የሖኑ ደሴቶች ያሏት አየርላንድ በየጊዜው የነበሯቸውን ነዋሪዎች እያጡ አሁን ላይ ወደ ምድረ በዳነት እየተቀየሩ ነው የተባለ ሲሆን በቀጣይ ወደ ደሴቶቹ የሚሄዱ ሰዎችን ለመጨመር አዲስ እቅድ ማውጧን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ እነዚህ ሰው አልባ የአየርላንድ ደሴቶች ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ድልድዮች እና መንገዶች የሏቸውም፡፡
ሀገሪቱ ወደደሴቶቹ ለሚያቀኑ አዳዲስ ነዋሪዎች ገንዘቡን በመስጠት ህይወት እንዲጀምሩ፣ ንብረቶችን እንዲያፈሩ እና ሌሎች ለህይወት አስፈላጊ የሖኑ ቁሳቁሶችን እንዲያሟሉባቸው የማድረግ እቅድ አላት ተብሏል፡፡
በዚህም መሰረት ከፈረንጆቹ ሀምሌ አንድ ጀምሮ ወደ አየርላንድ ደሴቶች በመሄድ መኖር የሚፈልጉ ዜጎች ማመልከት እንደሚችሉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የስፔን፣ ጣልያን እና ፊንላንድ መንግስታት ዜጎቻቸው ልጆችን እንዲወልዱ፣ ወደ ገጠር ከተሞች ሄደው እንዲኖሩ የተለያዩ የገንዘብ ስጦታዎችን ካዘጋጁ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡