ቻይና በታይዋን እና በሌሎች ሀገራት መካከል የሚደረግን ይፋዊ ግንኙነት በመደበኛነት ታወግዛለች
ቻይና ከታይዋን ጋር ይፋዊ ግንኙነት እንዳይመሰርቱ የአውሮፖ ሀገራትን አስጠንቅቃለች።
ቻይና፣ የአውሮፖ ሀገራት ከታይዋን ጋር ይፋዊ ግንኙነት እንዳያደርጉ ያስጠነቀቀችው የታይዋን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አውሮፖ ለመሄድ ማቀዳቸውን ተከትሎ ነው።
ቻይና፣ የአውሮፖ ሀገራት ከታይዋን ወይም ከታይዋን ነጻነት ኃይሎች ጋር ግንኙነት እንዳያደርጉ ነው ያስጠነቀቀችው።
የቼክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጃን ሊፖብስከመይ የታይዋን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዉ በሚቀጥለው ሳምንት ፖራጉን እንደሚጎበኙ አረጋግጠዋል።
ቻይና እንደራሷ ግዛት አድርጋ የምትመለከታት ታይዋን ከቫቲካን ውጭ ከአውሮፖ ሀገራት ጋር ይፋዊ ግንኙነት የላትም።
ቻይና በታይዋን እና በሌሎች ሀገራት መካከል የሚደረግን ይፋዊ ግንኙነት በመደበኛነት ታወግዛለች።
ቻይና ይህን የምታደርገው የታይዋንን ነጻ ሀገርነት በማበረታት የአንድ ቻይናን ሉአላዊነት ይጥሳል በሚል ምክንያት ነው።