እስራኤል በ“ኦሜክሮን” ምክንያት ዜጎቿ ወደ10 ሀገራት ጉዞ እንዳያደርጉ አገደች
በእስራኤል እስካሁን በኦሜክሮን የኮሮና ቫይረስ ዝርያ 86 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል
የጉዞ እገዳ ከተጣለባቸው ሀገራት የሚመጡ እስራኤላውያን በትንሹ ለ8 ቀናት ራሳቸውን ለይተው ማቆየት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል
የእስራኤል የጤና ሚኒስትር በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው ኦሜክሮን የተባለውን የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መስፋፋት ለመከላከል ወደ 10 ሀገራት የሚደረጉ እገዳዎችን ማገዷን አስታውቃለች፡፡
እገዳው ከመጭው ሮብእ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን የእስራኤል ዜጎች ጉዞ እንዳያደርጉባቸው የተባሉት ሀገራት ጣሊያን፣በቤልጄም፣ጀርመኒ፣ሀንጋሪ፣ሞሮኮ፣ፖርቱጋል፣ካናዳ፣ስዊቲዘርላንድ እና ቱርክ ናቸው፡፡ ሚኒስቴሩ እነዚህ ሀገራት አደገኛ የተጋላጭነት ደረጃ ላይ ናቸው ሲል መመደቡን ገልጿል፡፡
በኦሜክሮን ቫይረስ መስፋፋት አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሰዋል ከተባሉት ሀገራት መካከል ብዙ የአፍሪካ ሀገራት፣ስምንት የአውሮፓ ሀገራትና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ይገኙበታል፡፡
የጉዞ እገዳ ከተጣለባቸው ሀገራት የሚመጡ እስራኤላውያን የተከተቡና ያገገሙትን ጨምሮ በትንሹ ለ8 ቀናት ራሳቸውን ለይተው ማቆየት አለባቸው ተብሏል፡፡ በልዩ የመንግስት ኮሚቴ ከታየ የሰብአዊ ጉዳይ ውጭ፤የውጭ ዜጎች እግድ ከተጣለባቸው ሀገራት ወደ እስራኤል መግባት እንደማይችሉ ሚኒስትሩ ጠቅሷል፡፡
በእስራኤል እስካሁን ድረስ 134 ሰዎች በኦሜክሮን የኮሮና ቫይረስ ዝርያ የተጠቁባት ሲሆን ከእነዚህም መካከል 86ቱ ህይወታቸው አልፏል፡፡