የኔታንያሁ የፍርድ ሂደት በእሰራኤላውያን ዘንድ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል
የእስራኤል የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒሰትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተነግሯል።
ኔታንያሁ ፍርድ ቤት የቀረቡት በሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የአቃቤ ህግ ምስክር በአካል ተገኝተው ለማድመጥ እንደሆነም ተገልጿል።
እሳካለፈው ወርሃ ሰኔ ድረስ እስራኤልን ለ12 ዓመታት የመሩት ኔታንያሁ፤ ሲጋራ እና ሻምፓኝን ጨምሮ ስጦታዎችን በጉቦ መልክ ተቀብለዋል በሚል ነው የተከሰሰሱት።
እንዲሁም ለግል ገጽታ ግንባታ ለመገናኛ ብዙኃን ውለታ በመስራትና ጉቦ በመስጠት፣ እምነትን በማጉደል እና በማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ ናቸው ሲል አቀቤ ህግ ይከሳቸዋል።
የአስራኤል የቀድሞ ጠ/ሚኒሰትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በአቃቤ ህግ ለቀረበላቸው ክስ “ጥፋተኛ አይደለሁም” ሲሉ ከደው ተከራክረዋል።
የእስራኤል የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒሰትርና የአሁኑ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆነው ኔታንያሁ፣ ቃል አቀባይ እና የቅርብ አማካሪያቸው ኒር ሄፌትስ የሰጡትን ምስክርነት ለመስማት ወደ እየሩሳሌም ፍርድ ቤት ሲገቡ ፤በጥቁር የፊት ጭንብልው ስር ፈገግ ሲሉ መታየታቸው የችሎቱ አስገራሚ ክስተት ነበርም ተብለዋል።
“ኔታንያሁ በፀጥታ ጉዳዮች ላይ የሚያሳልፈውን ያህል ጊዜያቸውን በመገናኛ ብዙኃን ያሳልፉ ነበር፣ የውጭ ሰው ከንቱ ነው ብሎ በሚቆጥራቸው ጉዳዮች ላይም ጭምር” ሲሉም ነው ምስክርነታቸው የሰጡት ኒር ሄፌትስ።
የችሎት ውሎን ተከትሎ፤ የ72 አመቱ ኔታንያሁ በፍርድ ችሎት ላይ መገኘት እንዳልነበረባቸው የተነገረ ሲሆን፤ ምክንያቱ ደግሞ ችሎቶችን ተችተዋልና የሚሉ አስታየቶች በስፋት በመሰማቱ ነው።
ኔታንያሁ ወደ ችሎት ከመግባታቸው በፊት በርካታ ደጋፊወቻቸው በፍርድ ቤቱ ቅጥር ጊቢ ተገኝተው የድጋፍ ድምጽ ሲያሰሙ ነበር።
ኔታንያሁ ከችሎቱ በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን ምንም ከማለት ተቆጥበዋልም ነው የተባለው።
ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፤ ከወራት በፊት ወደ ስልጣን የመጡትን ናፍታሊ ቤኔት 36ኛው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሃላ እስከፈጸሙበት ድረስ የነበሩትን 12 ዓመታት የእስራኤል ሲመሩ የነበሩ አንጋፋ ፖለቲከኛ መሆናቸው ይታወቃል።