ጎርዶስ የተሰኘው ይህ ካፌ በቴልአቪቭ ታዋቂ እንደሆነ ተገልጿል
ጎርዶስ የተሰኘው የቼኮሌት ካፍቴሪያ በእስራኤል መዲና ቴልአቪቭ ከተማ ታዋቂ መሆኑ ይነገራል፡፡
የሀገሬው እና ጎብኚዎች የሚያዘወትሩት ይህ ካፌ ከሰሞኑ አነጋጋሪ ነገር ማድረጉን ተከትሎ አድናቆት እና ውግዘትን እያስተናገደ ይገኛል፡፡
ይህ ካፌ ለደንበኞቹ በመጸደጃ ቤት እቃ ቼኮሌት ማቅረብ መጀመሩን ተከትሎ ጉዳዩ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡
ካፌው በአብዛኛው በመጸዳጃ ቤት አገልግሎት ሲሰጥ በሚታወቀው እቃ ለደንበኞቹ ቼኮሌት ሲያቀርብ የሚያሳይ ምስል በኢንስታግራም ገጹ ላይ ማጋራቱን ተከትሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ አስተያየት አግኝቷል፡፡
አብዛኞቹ ኮሜንቱች ወይም አስተያየቶች የቁጣ መልክ ያላቸው ሲሆኑ ካፌው ግን እስካሁን ምንም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡
ለካፌው ከተሰጡት ኮሜንቶች መካከል ይህ ቼኮሌት አይመስልም፣ እጅግ በጣም ዘጊ ነው የሚለው አንዱ ሲሆን ሌላኛው ኮሜንት ደግሞ ይህ ካፌ ምን ያህል የደንበኞች እጥረት ቢያጋጥመው ነው ይህን መሳይ አገልግሎት ለመስጠት የወሰነው ይላል፡፡
በተጨማሪም እስራኤል ከ50 በመቶ በላይ ሀይማኖተኞች የሚኖሩባት ሀገር ነች፣ ድርጊቱ የሀገርን ባህል እና ሀይማኖትን እንደማዋረድ ይቆጠራል የሚል አስተያየትም ተሰጥቷል፡፡
ሌላኛው ኮሜንት ደግሞ ካፍቴሪያው በመክሰር ላይ ባይሆን ይህን ያህል የሰዎችን ትኩረት ለማግኘት ሲል አስቀያሚ ማታወቂያ አይጠቀምም ነበር የሚል ነው፡፡
በማስታወቂያው ዙሪያ ካፍተሪያውም ሆነ ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት እስካሁን ያሉት ነገር የለም፡፡