25ኛ ቀኑን በያዘው የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ምን አዳዲስ ነገሮች ተከስተዋል?
እስራኤል አዳሩን በጋዛ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ቢያን 40 ሰዎች ሞተዋል
ሃማስ ቡድን ተዋጊዎች ብዙ ታንኮችን እንዳወደሙና የእስራኤልን ግስጋሴ እንደገቱ ይናገራሉ
ሃማስ እስራኤል ያልተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት 25 ቀናትን አስቆጥሯል።
እስራኤል ወደ ሁለተኛ ምእራፍ ተሸጋግሯል ባለችው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በእግረኛ ጦር፣ በብረት ለበስ እና በአየር አጠናክራ ቀጥላለች።
ሃማስም ወደ እስራኤል ሮክት መረኮሱን የቀጠለ ሲሆን፤ በትናትናው እለት የተኮሰው ሮኬት በእስራኤል ውድመት አድርሷል።
በ25ኛ ቀን የተስተናገዱ ክስተቶች በጥቂቱ
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደች ባለው የእግረኛ ጦር ዘመቻ በሀማስ ተይዛ የነበረችውን ወታደር ማስለቀቋን አስታውቃለች።
አዳሩን በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ድብደባ ሲደረግ አድሯል፤ በእስራኤል የአየር ድብደባ ሌሊቱን 40 ፍሊስጤማውያን ተገድለዋል።
የእስራኤል ሃይሎች በዌስት ባንክ የሚገኘውን የሐማስ ከፍተኛ መሪ ሳሌህ አል አሮሪን መኖሪያ ቤትን ማፈንዳታቸው ተነግሯል።
ማክሰኞ ማለዳ ላይ የእስራኤል ጦር ተዋጊ ጄቶች በሊባኖስ ውስጥ የሂዝቦላህን “መሰረተ ልማት” መትተዋል።
በጋዛ ሰርጥ ሆስፒታሎች ኢላማ መደረጋቸው ቀጥለዋል፤ በሰሜን ጋዛ የሚገኙት አል ቁድስ እና የኢንዶኔዢያ ሆስፒታል የአየር ድብደባ እና በመድፍ ተመትተዋል።
የቱርክ-ፍልስጤም ወዳጅነት ሆስፒታል ከባድ የአየር ጥቃቶች ተፈጽመውበታል፤ ዛሬ ጠዋት ላይ ላይ በደቡባዊ ጋዛ የሚገኘው የአውሮፓ ሆስፒታል በአየር ጥቃት መመታቱንም ሮይተርስ ዘግቧል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሃማስ የሶስት ታጋቾችን ምስል መልቀቁን ተከትሎ በሰጡት አስተያጠ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነትን በመቃወም ይህ “የጦርነት ጊዜ ነው” ሲሉ አውጀዋል።
በሰሜን ጋዛ በእስራኤል ጦር እና በሃማስ ታጠቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን፤ በተለይም በሰሜን ጋዛ በተለያዩ ግንባሮች ውጊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
እስራኤል በእግረኛ ጦር፣ በብረት ለበስ እና በአየር አጠናክራ ቀጥላለች፤ የእስራኤል ታንኮች ወደ ጋዛ ከተማ ዘልቀው ለመግባት ሞክረዋል።
የፍሊስጤሙ ሃማስ ቡድን ተዋጊዎች ብዙ ታንኮችን እንዳወደሙ እና የእስራኤልን ግስጋሴ እንደገቱ ይናገራሉ።
እስራኤል እየወሰደችው ባለው የአጻፋ እርምጃም ከ8 ሺህ 500 በላይ ፍልስጤማውያን ህይወት መቀጠፉን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከሞቱ ሰዎች መካከልም ከ3 ሺህ በላይ ህጻናት፤ 2 ሺህ ደግሞ ሴቶች ናቸው ሲሆኑ፤ ከ20 ሺህ በላይ ፍሊስጤማውያን ቆስለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር በጋዛ በየቀኑ ከ420 በላይ ህጻናት ይገደላሉ ወይም ይቆስላሉ ሲሉ አስታውቀዋል።