ሚሊየኖችን ያፈናቀለውና ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስን ያስከተለው ጦርነት ከመብረድ ይልቅ ተባብሶ ቀጥሏል
ሃማስ ወደ እስራኤል ያልተጠበቀ ጥቃት ከፈጸመ 21 ቀናት ተቆጥረዋል።
እስራኤል እየወሰደችው ባለው የአጻፋ እርምጃም ከ7 ሺህ 700 በላይ ፍልስጤማውያን ህይወት መቀጠፉን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሃማስ ከእስራኤል አግቶ የወሰዳቸውን ከ200 በላይ ሰዎች ካልለቀቀ ውሃ፣ መብራትና ነዳጅ ወደ ጋዛ አልክም ያለችው ቴል አቪቭ ጋዛን እያፈራረሰች ነው።
2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሰዎች ተጠጋግተው የሚኖሩባት ጋዛ በከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ ውስጥ ናት።
ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎቿ ከመኖሪያቸው ቢፈናቀሉም የደህንነት ዋስትና አላገኙም።
በግብጽ ራፋህ ድንበር መተላለፊያ በኩል እየገባ ያለው ሰብአዊ ድጋፍም ከሚያስፈልገው አንጻር እጅግ በጣም አነስተኛ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት ገልጿል።
ከሶስት ሳምንት በፊት የተጀመረው የእስራኤልና ሃማስ ጦርነት ያስከተለውን ጉዳት በአሃዝ ይመልከቱ፦