እስራኤል በሀማስ ተይዛ የነበረችውን ወታደር ማስለቀቋን አስታወቀች
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ እስራኤል የሰብአዊ ተኩስ አቀም እንድታደርግ ቢወስንም፣ እሰራኤል ግን አሻፈረኝ ብላለች
ሀማስ በጫና ውስጥ ካልገባ ታጋቾችን እንደማይለቅ የተናገሩት ኔታንያሁ ሁሉንም ወደ ቤታቸው ለመመለስ ዘመቻው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል
እስራኤል በሀማስ ተይዛ የነበረችውን ወታደር ማስለቀቋን አስታወቀች።
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደች ባለው የእግረኛ ጦር ዘመቻ በሀማስ ተይዛ የነበረችውን ወታደር ማስለቀቋን አስታውቃለች።
ኦሪ መግዲሽ የባለችውን ወታደር ሀማስ በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ጥቃት በሰነዘረበት ጊዜ ነበር የወሰዳት።
ወታደሯ አሁን ላይ ህክምና እንደተደረገላት እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የእስራኤል ጦር ገልጿል።
እስራኤል እንደምትለው ከሆነ ሀማስ 200 በላይ ሰዎችን ይዟል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እስራኤል በሀማስ ላይ እየወሰደችው ያለው እርምጃ ሁለተኛ ምዕራፍ ላይ መድረሱን እና ታጋቾችን የማስለቀቅ እድሉ የሰፋ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ሀማስ በጫና ውስጥ ካልገባ ታጋቾችን እንደማይለቅ የተናገሩት ኔታንያሁ ሁሉንም ወደ ቤታቸው ለመመለስ ዘመቻው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በጋዛ የገባው የእስራኤል ጦር ይዞታውን እያስፋፋ እና ዘመቻውን እያጠናከረ እንደሚቀጥል የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሀጋሪ በትናንትናው እለት መናገራቸው ይታወሳል።
ሀማስ ከወታደሯ ቀደም ብሎ አራት ታጋቾችን በመልቀቅ ከእስራኤል ጋር ለመነጋገር እንደሚፈልግ ገልጾ ነበር።ነገርግን እስራኤል የጀመረችውን ዘመቻ አጠናክራ በመቀጠሏ ሀማስም ለመልሶ ማጥቃት በሙሉ አቅሙ መዘጋጀቱን ገልጿል።
እስራኤል የሀማስ ይዞታ የሆነችውን ጋዛን ከበባ ውስጥ በማስገባቷ ምክንያት ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ ተከስቷል።
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ እስራኤል የሰብአዊ ተኩስ አቀም እንድታደርግ ቢወስንም፣ እሰራኤል ግን አሻፈረኝ ብላለች።