አንድ ዓመት የሞላው የእስራኤል -ሐማስ ጦርነት በእስራኤል ላይ ስላደረሰው ጉዳት ቁጥሮች ምን ይላሉ?
726 የእስራኤል ወታሮች ሲሞቱ፤ ከ4 ሺህ 800 በላይ ወታደሮች ቆስለዋል
13 ሺህ 200 ሮኬቶች ከጋዛ፤ 12 ሺህ 400 ሮኬቶች ከሊባኖስ ወደ እስራኤል ተተኩሰዋል
ከተጀመረ ዛሬ ድፍን አንድ ዓመት በሞላው የሃማስ ጦርነት በርካታ ሰብዓዊ ቀውስችን እያስከተለ እንደቀጠለ ይገኛል።
የጋዛው ሃማስ በእስራኤል ላይ የዛሬ ዓመት መስከረም 27 2016 ወይም በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 2023 የተቀናጀና ድንገተኛ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ነው ጦርነቱ የተከሰተው።
ይህንን ተከትሎም የእስራኤል ጦር ባለፈው አንድ ዓመት ጦሩ እንዲሁም እስራኤል ላይ የደረሱ ጉዳቶችን እና እሱን ለመበቀል በወሰዳቸው እርጃዎች ዙሪያ መረጃ አጋርቷል።
ጦሩ ባጋራው መረጃም የጋዛው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የሞቱ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 726 መድረሱን እና ከእነዚህም ውስጥ 380 ወታሮች የሃማስ ድንገተኛ ጥቃት በፈተጸመበት እለት ሲሞቱ፤ 346 ወታሮች ደግሞ ከ20 ቀናት በኋላ ጋዛ ውስጥ መካሄድ በጀመረው የእግረኛ ጦር ኦፕሬሽን ወቅት መሞታቸውን አስታውቋል።
በጦርነት ላይ ከሞቱ ወታሮች በተጨማሪም 56 የእስራኤል ጦር አባላት ስፍራው እና ቀኑ ባልተገለጸ አደጋ መሞታቸውን ነው ጦሩ ያስታወቀው።
የእስራኤል ጦር በመግለጫው አክሎም ጦርቱ ከተጀመረ ወዲህ ከ4 ሺህ 800 በላይ ወታደሮቹ በጦርነቱ ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸውም አስታውቋል።
በሲቪል ሰዎች ላይ በደረሰው ጉዳትም 1 ሺህ 677 የእስራኤል ዜጎች ሲገደሉ፤ ከ250 ሰዎች በሃማስ ታግተዋል፤ ከእነዚህም ውስጥ 100 ያክሉ እስራኤላውያን አሁንም በሃማስ እገታ ስር ይገኛሉ።
ጦርነቱን ተከትሎ በእስራኤል ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች
የእስራኤል ጦር የጋዛው ጦርነት ከተጀመረ እለት አንስቶ በእስራኤል ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የሮኬት እና የሚሳዔል ጥቃቶች እንደተፈከቱበት አስታውቋል።
ከእነዚህም መውስጥ
-13 ሺህ 200 ሮኬቶች- ከጋዛ
-12 ሺህ 400 ሮኬቶች- ከሊባኖስ
-400 ሚሳኤልና ድሮኖች- ከኢራን
-180 ሚሳኤልና ሮኬቶች- ከየመን
-60 ሮኬቶች- ከሶሪያ ወደ እስራኤል ተተኩሰዋል።
እስራኤል ያስተናገደችው የኢኮኖሚ ኪሳራ ምን ይመስላል?
እስራኤል ጋዝን ጨምሮ በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ሀገራት የምትፈጽመው ጥቃት በኢኮኖሚያዋ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ይገኛል።
የጋዛው ጦርነት ከተጀመረበት እለት አንስቶ እስካሁን ባለው ጊዜ እስራኤል 66 ቢሊየን ዶላር ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እንደደረሰባትም ተነግሯል።
የእስራል የፋይናንስ ሚንስተር ቤዛለል ስሞትሪች ሀገሪቱ በታሪኳ ውዱ የሆነውን ጦርነት እያካሄደች ነው ብለዋል።
እስራኤል የተፈጸሙባን ጥቃቶች ለመከላከል ምን አደረገች
የእስራል ጦር ባለፈው አንድ ዓመት የተከፈተበትን ጥቃት ለመከላል ከ40 ሺህ በላይ ኢላማዎችን መምታቱን፣ 4 ሺህ 700 የመሬት ውስጥ ዋሻዎችን ማግኘቱን እና 1 ሺህ የሮኬት ማስወንጨፊጠያ ስፍራዎችን ማውደሙን አስታውቋል።
ጦርነቱ ከተጀመረበት እለት ጀምሮ ከ300 ሺህ በላይ ተጠባባቂ ወታሮችን መቅጠሩን ያስታወቀው የእስራኤል ጦር፤ እነዚህም እድሜያቸው ከ20 እስከ 29 መካከል የሚገኝ እና 82 በመቶ ወንድ እንዲሁም 18 በመቶ ሴቶች ናቸው ብሏል የእሳኤል ጦር በመግለጫው።
የእስራኤል ጦር በጋዛ ብቻ በፈጸማቸው የአየር ጥቃቶች እና ወታደራዊ ዘመቻዎች የሞቱ የፍሊስጤማውያን ቁጥርም ከ42 ሺህ ማለፉን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።