አንድ ዓመት የሞላው የእስራኤል -ሐማስ ጦርነት እና የደረሰው ውድመት
በጦርነቱ ከተገደሉት 42 ሺህ ፍልስጤማዊያን መካከል 60 በመቶዎቹ ህጻናት እና ሴቶች ናቸው
ከ800 በላይ ሐኪሞች እና 173 ጋዜጠኞች በእስራኤል ተገድለዋል
አንድ ዓመት የሞላው የእስራኤል -ሐማስ ጦርነት እና የደረሰው ውድመት
ለፍልስጤም ነጻነት የሚታገለው ሐማስ በእራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረው ጦርነት አንድ ዓመት ሞልቶታል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚህ ጦርነት የደረሱ ጉዳቶችን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት በፍልስጤም በኩል 41 ሺህ 788 ንጹሃን ሲገደሉ በእስራኤል በኩል ደግሞ 1 ሺህ 677 ዜጎች ተገድለዋል፡፡
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በፍልስጤም በኩል ከተገደሉት አጠቃላይ ሟቾች ውስጥ 60 በመቶው ሴቶች እና ህጻናት ናቸው፡፡
እንዲሁም 96 ሺህ 794 ሰዎች በእስራኤል ጥቃት ሲቆስሉ 16 ሺህ ህጻናት እና 11 ሺህ ሴቶችም መገደላቸው ተገልጿል፡፡
እስራኤል የኢራንን ሚሳኤል ለማክሸፍ ከ450 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጓ ተገለጸ
በጥቃቱ 885 ሐኪሞችን ጨምሮ 173 ጋዜጠኞች፣ 710 ጨቅላ ህጻናት ሲገደሉ 19 ሺህ ህጻናት ወላጅ አልባ ሆነዋልም ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም 115 ተመራማሪዎች፣ የዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች እና አጥኚዎችም በእስራኤል ተገድለዋል፡፡
በአጠቃላይ እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው ጥቃት 718 ሺህ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ሲሆኑ 2 ሚሊዮን ዜጎች ከቤታው ተፈናቅለዋል፡፡
በእስራኤል በኩል ደግሞ 1ሺህ 677 ሰዎች ሲገደሉ 18, ሺህ 225 ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያ ቤታቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡
እስራኤል በጋዛ ባደረገችው ዘመቻ 724 ወታደሮቿ ሲገደሉባት 4 ሺህ 480 ደግሞ ቆስለውባታል ተብሏል፡፡
በእስራኤል ላይ 18 ሺህ ሮኬቶች ከየመን፣ ከጋዛ፣ ኢራን፣ ኢራቅ እና ከሊባኖስ እንደተተኮሱባት ተገልጿል፡፡