በእስራኤል-ሄዝቦላህ ጦርነት ዙሪያ ምን አዳዲ ክስተቶች አሉ? እስካሁን የምናውቀው…
ሄዝቦላህ በእስራኤል ጦር ታንኮች ላይ የተሳካ ጥቃት መሰንዘሩን እታውቋል
እስራኤል ጥቃት የሞቱ ሊባኖሳውያን ቁትር ከ2 ሺህ ማለፉን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል
በእስራኤልና በሊባኖሱ ሄዝቦላህ መካከል የነበረው ግጭት እየተካረረ መጥቶ አሁን ላይ ወደ ሙሉ ጦርነት ተሸጋግሯል።
ተባብሶ በቀጠለው የሄዝቦላህ እና እስራኤል ጦርነት ከእስራኤል የአየር ድብደባ በተጨማሪ የፊትለፊት የምድር ላይ ውጊያም ቀጥሏል።
ምን አዳዲስ ክስተቶች ተስተናግደዋል?
-የእስራኤል ጦር ነዋሪዎች እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተከትሎ ትናነት አዳሩን እና ዛሬ ጠዋት በቤሩትና በሌሎች የሊባኖስ አካባቢዎች የአየር ድብደባዉን ቀጥሏል።
-ቤሩት የጦርነት ቀጠና እየሆነች ነው የተባለ ሲሆን፤ ትናንት አዳሩን ከ12 በላይ የአየር ድብደባዎች ተፈጽመውባታል፤ ዛሬም ድብደባው ቀጥሏል።
-በሰሜን ሊባኖሷ ትሪፖሊ ከተማ በእስራኤል በተፈተመ የአየር ድብደባ አንድ የሃማስ ወታደራዊ አመራር ከባለቤቱና እና ከሁለት ልጆቹ ጋር ተገድሏል።
-ሄዝቦላህ ሌሊቱን ከእስራኤል የተከፈተበትን ጦርነት መመከቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ የምድር ላይ ውጊያ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።
-ሄዝቦላህ ተዋጊዎቹ የፀረ ታንክ ሚሳዔል በመጠቀም የእስራኤል መርካቫ ታንክ ማውደሙን እና ታንከኛ ወታደሮችንም መግደሉን አስታውቋል።
-ሄዝቦላህ በዛሬው እለት ብቻ በሊባኖስ ወረራ ለማስፋፋት እየመኮረ ባለ የእስራኤል ጦር ላይ ሰባት የተሳኩ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታውቋል።
ሄዝቦላህ ፋዲ-1 የተባለ ሚሳዔል በመጠቀም ከሊባኖስ ድንበር 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የእስራኤል ጦር ካምፕ ላይ ጥቃት መሰንዘሩንም ገልጿል።
-የሊባኖሱ ቡድን ሄዝቦላህ በድንብር አካባቢ ባሉ የእስራኤል ጦር ላይ በርካታ ሮኬቶችን መተኮሱንም ነው ያስታወቀው።
- የሊባስ ጤና ሚኒስቴር እስራኤል እስካሁን በመላው ሊባኖስ ባደረገቸው የአየር ድብደባ ከ2 ሺህ በላ ሰዎች ተገድለዋል ሲሆን፤ ከእነዚህም 127 ህጻነት እና 261 ሴቶች ይገኙበታል።