እስራኤል የጋዛ ነዋሪዎችን በድጋሚ አስጠነቀቀች
እስራኤል ጋዛውያን ወደ ደቡብ የማይሄዱ ከሆነ እንደሽብርተኛ ተባባሪ ሆነው እንደሚታዩ በድጋሚ ማስጠንቀቋ ተገልጿል
ሀማስ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት ካደረሰበት ከጥቅምት የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ እስራኤል ጋዛን በአየር እየደበደበች ትገኛለች
እስራኤል የጋዛ ነዋሪዎችን በድጋሚ አስጠነቀቀች።
እስራኤል ጋዛውያን ወደ ደቡብ የማይሄዱ ከሆነ እንደሽብርተኛ ተባባሪ ሆነው እንደሚታዩ በድጋሚ ማስጠንቀቋ ተገልጿል።
የጋዛ ነዋሪዎች እንደገለጹት የእስራኤል ጦር ወደ ደቡብ የጋዛ ክፍል እንዲሆዱ ማስጠንቀቁን እና የማይሄዱ ከሆነ "የሽብርተኛ ድርጅት" ተባባሪ አድርጎ እንደሚመለከታቸው መግለጹን ነግሯቸዋል።
ማስጠንቀቂያው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ስም እና ሎጎ አርፎበት በተበተነ ወረቀት የተሰራጨ መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
"ለጋዛ ነዋሪዎች አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ። ከዋዲ ጋዛ በሰሜን በኩል መኖራችሁ ህይወታችሁን አደጋ ላይ ይጥለዋል። ማንኛውም ዋዲ ጋዛን አልፎ የማይሄድ ሁሉ የሽብርተኛ ድርጅት ተባባሪ ተደርጎ ይታያል" ይላል በራሪ ጹሁፉ።
ሀማስ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት ካደረሰበት ከጥቅምት የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ እስራኤል ጋዛን በአየር እየደበደበች ትገኛለች።
እስራኤል በእግረኛ ወታደር ጥቃት ለመክፈት ብዙ ቀጥር ያለው ወታደር እና ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ከጋዛ በሚያዋስናት ድንበር በኩል አከማችታለች።
የእስራኤል ጦር ቀደም ሲልም የጋዛ ነዋሪዎች ከሰሜን ወደ ደቡብ እንዲሄዱ አስጠንቅቆ ነበር።
የመጀመሪያውን የእራኤል ለቃችሁ ውጡ ማስጠንቀቂያ ሰምተው ወደ ደቡብ ጋዛ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች የአየር ጥቃት እንደደረሰባቸው እና ጉዞው አስፈሪ መሆኑን ይገልጻሉ።
የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት እንዲቆሙ የሚደረጉ ጥረቶች አስካሁን ውጤታማ አልሆኑም።