ፕሬዝዳንት ባይደን የነደፉት ብሄራዊ ደህንነት ህግ ከሁሉም ድጋፍ እንደሚያገኝ ተስፋ ይዘዋል
ዋይት ሀውስ የዩክሬን፣ እስራኤል እና የአሜሪካ የደህንነት እቅዶችን ለመደገፍ 106 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቋል።
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የገንዘብ ጥያቄ እስራኤልን ከጎበኙና ትብብር ለማድረግ ቃል በገቡ ከቀናት በኋላ የመጣ ነው።
እስራኤልና ከዩክሬን፣ ከድንበር ደህንነት፣ ከስደተኞች እርዳታ፣ የቻይና መገዳደሪያ እርምጃዎች እና ሌሎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ጋር የመደቡት ፕሬዝዳንቱ፤ ድጋፍ የሚያገኝ የብሄራዊ ደህንነት ህግ እንደነደፉ ተስፋ ሰንቀዋል።
ባይደን በተጨማሪም ለእስራኤል እና ጋዛ ጨምሮ ለሰብዓዊ እርዳታ ከዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሹ ተነግሯል።
ባለፈው ዓመት ሪፐብሊካኖች የተቆጣጠሩት ም/ቤቱ መሪ አልባ ሆኖ ለ18 ቀናት ቆይቷል።
አንዳንድ የሪፐብሊካን የህግ አውጭ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ጦርነት በገንዘብ መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን እየተጠራጠሩ ናቸው ተብሏል።
ስር የሰደደውን የአሜሪካ የበጀት ጉድለት ለማስቆም መንግስትን ሙሉ በሙሉ ለመዝጋትም ዝተዋል።
የባይደን የበጀት ዳይሬክተር የአሜሪካ ህዝብ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መሪዎቻቸው በአንድነት ተሰባስበው እንዲፈጽሙ ይጠብቃሉ ብለዋል።
ኃላፊዋ በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ገንዘቡን ኮንግረሱ አጠቃላይ የሁለትዮሽ ስምምነት አካል አድርጎ እንዲመለከተውም ጠይቀዋል።