እስራኤል በደርዘን የሚቆጠሩ የሀማስ ተዋጊዎችን መግደሏን አስታወቀች
ጥቃቱ እስራኤል እየወሰደች ያለውን ጥቃት የማቀዝቀዝ ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳይ ነው ተብሏል
እስራኤል ድንበሯን በመጣስ 1400 ዜጎቿን በገደለባት ሀማስ ላይ እየወሰደች ያለውን የአጸፋ ጥቃት ቀጥላበታለች
እስራኤል በደርዘን የሚቆጠሩ የሀማስ ተዋጊዎችን መግደሏን አስታወቀች።
እስራኤል በዛሬው እለት እንዳስታወቀችው በጋዛ ላይ ባካሄደችው የአየር ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ የሀማስ ታጣቂዎችን ገድላለች።
ጥቃቱ እስራኤል እየወሰደች ያለውን ጥቃት የማቀዝቀዝ ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
አሜሪካ፣ ለሁለት ሳምንታት ከበባ ውስጥ ያሉት የጋዛ ነዋሪዎች እርዳታ እንዲገባላቸው እስራኤልን እየጠየቀች መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ታሪክ ውስጥ እጅግ ደምአፋሳሽ ነው የተባለው ይህ ግጭት ወደ ተኩስ አቁም የሚያመራበት እድል ጠባብ ነው።
እስራኤል ድንበሯን በመጣስ 1400 ዜጎቿን በገደለባት ሀማስ ላይ እየወሰደች ያለውን የአጸፋ ጥቃት ቀጥላበታለች።
የጋዜ የጤና ሚኒስቴር በእስራኤል የአየር ጥቃት የተገደሉ ሰዎች 5000 መድረሱን ገልጿል። ሀማስ ጥቅምት መጀመሪያ ሳምንት ባደረሰው ጥቃት አግቶ ከወሰዳቸው 200 ሰዎች መካከል ሁለት እስራኤላውያንን ሰኞ እለት ለቋል። ሀማስ ቀደም ሲል አሜሪካውያን እናት እና ልጅም መልቀቁ ይታወሳል።
የሀማስ ታጣቂዎችን ከምድረ ገጹ ለማጥፋት የዛተችው እስራኤል በጋዛ በእግረኛ ወታደር ጥቃት ለመክፈት ተዘጋጅታለች።በጋዛ ዙሪያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር አከማችታለች።
የአረብ ሀገራት ገጭቱ እንዲቆም እየጠየቁ ሲሆን ምዕራባውያን ሀገራት ግን ስለሰብአዊ ሁኔታው ብቻ ማተኮርን መርጠዋል።