እስራኤልና ኮሶቮ ስምምነቱ እንዲፈረም አሜሪካ አስተዋጽኦ አድርጋለች ብለዋል
በዙም ቴክኖሎጂ በመታገዝ በበይነ መረብ ባካሄዱት ስብሰባ እስራኤልና ኮሶቮ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመስረት የሚያስችላቸውን ታሪካዊ የተባለ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋሃቢ አሽከናዚ ከእየሩሳሌም ሆነው እንደተናገሩት ይህ በዙም የተፈረመ የዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ነው ብለዋል፡፡
የኮሶቮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሊሳ ሃራዲናጃ ስቱብላ ስምምነት የተፈረመበት ቀን ታሪካዊ ቀን ነው ተብሏል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ እንደገለጹት ስምምነቱ ከእአስራኤል ጋር ጠንካራ ስምምነት ለመመሰረት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በእስረኤል በኩል አሽኬናዚ በኮሶቮ በኩል ደግሞ ስቱብላ የፖለቲካ ምክክር ለማድረግ የሚያስችልና የሁለትዮሽ ትብብር ለማምጣት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደገለጹት ስምምነቱ ለሁለቱም አካል በኢሜል ተልኮ እንዲፈርሙበት ይደረጋል ብለዋል፡፡ ለስምምነቱ መፈረም አስተዋፅኦ ያደረገችው አሜሪካ በተወካይዋ በኩል ተገኝታለች፡፡
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ” ዛሬ ታሪክ ስርተናል፡፡ በእስራኤልና በከሶቮ መካከል ሲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መስርተናል፤ ይህም እኔ እንደሚመስለኝ በዙም ቴክነሎጂ የተፈረመ የመጀመሪያው ስምምነት ነው ” ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ አሜሪካ ሰላምን ለመፍጠር ላደረገችው ጥረት አመስግነዋል፡፡ በእስራኤልና በኮሶቮ መካከል የተፈረመው ስምምነት በቀጣናው ለውጥ መምጣቱን እንደሚያመለክት ገልጸዋል፡፡
የእስራኤሉ ሚኒስትር እንዳሉት ዛሬ በኮሶቮ በኩል ኢምባሲ ልክፈት ተብሎ የቀረበውን ጥያቄ ተቀብያለሁ፤ በቅርቡም ይከፈታል፡፡
አሽኬናዚ እንደተናገሩት እስራኤልና ኮሶቮ በኢኮኖሚ፣በቱሪዝም፣በባህልና በሌሎች መስኮች ስምምነት ይፈራረማሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
አሽኬናዚና የኮሶቮ አቻቸው አሜሪካ ይህ ስምምነት እንዲፈም ላደረገችው አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡ የኮሶቮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስቱብላ እስራኤል የኮሶቮን ነጻ ሀገርነት እውቅና የሰጠች 117ኛ ሀገር ናት ብለዋል፡፡