ፍልስጤም ቴላቪቭ ለሰብዓዊ እርዳታ ሙሉ ለሙሉ ተኩስ እንድታቆም ዓለም አቀፍ መሪዎች ግፊት እንዲያደርጉ ጠየቀች
እስራኤል በጋዛ ላይ 'የበቀል ጦርነት' እያካሄደች ነው- ፍልስጤም
እስራኤል በጋዛ ላይ ሙሉ ለሙሉ ውድመትን ያነጣጠረ "የበቀል ጦርነት" እያካሄደች ነው ሲሉ የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ከሰዋል።
የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሪያድ አል-ማሊኪ "[በጋዛ] በጣም ብዙ ጦርነቶች ተካሂደዋል። ይህ ግን የተለየ ነው። በዚህ ጊዜ የበቀል ጦርነት ነው" ሲሉ በሄግ ለጋዜጠኞች ተናግሯል።
ሚንስትሩ "ይህ ጦርነት በጋዛ ውስጥ ያሉ የመኖሪያ ቦታዎችን በሙሉ ከመደምሰስ ውጭ ምንም አይነት ተጨባጭ ዓላማ የለውም" በማለት አክለዋል።
ሁሉም ዓለም አቀፍ የጦርነት ህጎች ተጥሰዋል ያሉት ሪያድ አል-ማሊኪ፤ ጦርነቱ በወታደራዊ እቅድ እየተመራ አይደለም ሲሉም ተችተዋል።
እስራኤል በሀማስ ለታገቱባት ዜጎቿ መረጃ ለሚሰጧት ጉርሻ አቀረበች
ጋዛ ለሦስት ሳምንታት ለሚጠጋ ጊዜ በእስራኤል የቦምብ ናዳ እየዘነበባት ነው።
ከሀማስ ለደረሰባት ጥቃት ምላሽ እየሰጠች ያለችው እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ተናገረች።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ ዓለም አቀፍ መሪዎች እስራኤል ሙሉ ለሙሉ ተኩስ እንድታቆም ግፊት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።
ሚንስትሩ ከጎርጎሮሳዊያኑ 2014 ጀምሮ በፍልስጤም ግዛት ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ የጦር ወንጀሎችን እየመረመረ ያለውን ዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍ/ቤት ጎብኝተዋል።