እስራኤል ፍልስጤማዊያንን ወደ ደቡብ እንዲሸሹ ካዘዘች በኋላ ለምን ደቡብ ጋዛን ታጠቃለች?
ቴላቪቭ በደቡብ ጋዛ የተለያዩ ኢላማዎች እየደበደበች ነው ተብሏል
የእስራኤል ጦር ሀማስ በህዝቡ ውስጥ ስር የሰደደ መሆኑን ተናግሯል
እስራኤል ፍልስጤማዊያንን ወደ ደቡብ እንዲሸሹ ካዘዘች በኋላ ለምን ደቡብ ጋዛን ታጠቃለች?
እስራኤል በሰሜናዊው የጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ሲቪሎች ለደህንነታቸው ሲሉ ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሄዱ ትዕዛዝ አስተላልፋለች።
የሀገሪቱ ጦር ትዕዛዙ ሀማስ ላደረሰው ጥቃት የመልስ ምት ለመስጠት በሚያደርገው ጥቃት ንጹሀንን ለመጠበቅ እንደሆነ ተናግሯል።
ይሁን እንጂ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በደቡባዊ ጋዛ የሚገኙ ቦታዎችን መምታታቸውን ቀጥለዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህም ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ለጥቃት እንጋለጣለን የሚል ፍራቻ ፈጥሮባቸው ተብሏል።
የእስራኤል ጦር ጋዛውያን ወደ ደቡብ እንዲሄዱ ካሳወቀ ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው ያሉትን ኢላማዎች እየደበደበ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሲቪሎችን መግደሉ ተነግሯል።
የጋዛ ባለስልጣናት የእስራኤል ጥቃት ከጀመረ በኋላ ስድስት ሽህ 546 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል ብለዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው በደቡብ ላይ የሚካሄደው የቦምብ ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የሀገራት የሀይል አሰላለፍ ምን ይመስላል?
ከግብፅ ድንበር 10 ኪሜ እርቀት ላይ በምትገኘው በካን ዮኒስ ውስጥ በርካታ የመኖሪያ ህንጻዎች ወድመዋል።
የመከላከያ ኃይሉ የሀማስ ዋና የኃይል ማዕከል በጋዛ ከተማ ቢሆንም እንኳን በህዝቡ ውስጥ ስር የሰደደ መሆኑን ተናግሯል።
"የሀማስ ኢላማ በተገኘበት ቦታ ሁሉ የመከላከያ ሰራዊት የቡድኑን የአሸባሪነት አቅም ለማክሸፍ ይደበድባል" በማለት ጦሩ ተናግሯል።
በሌላ በኩል በግጭቱ ያልተሳተፉ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቅረፍ ተጨባጭ ጥንቃቄዎችን እያደረገ መሆኑን ገልጿል።