እስራኤላዊያን ያዘኑበት የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ወንድ ልጅ የት ነው ያለው?
ከ360 ሺህ በላይ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የእስራኤል ተጠባባቂ ወታደሮች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወንድ ልጅ ዬር ንታንያሁ እስካሁን ወደ እስራኤል አለመመለሱን በርካቶች እየተቹ ይገኛሉ
እስራኤላዊያን ያዘኑበት የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ወንድ ልጅ የት ነው ያለው?
ከ20 ቀናት በፊት ለፍስልጤም ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሐማስ በእስራኤል ላይ ያልታሰበ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በአካባቢው ጦርነት ተቀስቅሷል፡፡
እስካሁን የዓለም ዋነኛ የትኩረት አጀንዳ የሆነው ይህ ጦርነት መቋጫ ይልተገኘለት ሲሆን በውጭ ሀገራት ይኖሩ የነበሩ እስራኤላዊያን ለሀገራቸው ለመዋጋት በመመለስ ላይ ናቸው፡፡
ሁሉም እስራኤላዊ የሀገሩ ተጠባባቂ ጦር አባል ሲሆን እስካሁን ከ360 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል፡፡
ይህ ሁሉ እስራኤላዊ ለሀገሩ ለመዋጋት እየተመለሰ ባለበት ወቅት የጠቅላይ ሚኒስት ቤንያሚን ኔታንያሁ ወንድ ልጅ የሆነው ዬር ኔታንያሁ ወደ ሀገሩ አልተመለሰም ተብሏል፡፡
ይህን ተከትሎም በርካታ እስራኤላዊያን ለምን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ ከውጊያ ፊት አልተገኘም ሲሉ ትችቶችን በመሰንዘር ላይ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
እስራኤል በሀማስ ለታገቱባት ዜጎቿ መረጃ ለሚሰጧት ጉርሻ አቀረበች
የ32 ዓመቱ ዬር ኔታንያሁ ካሳለፍነው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ወደ አሜሪካዋ ፍሎሪዳ ተጉዞ እየኖረ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ በሚያሚ የባህር ዳርቻ ሲዝናና መታየቱን ተከትሎ ትችቶችን በራሱ እና በአባቱ ላይ እንዲነሳ አድርጓል፡፡
በርካቶች የጫጉላ ሽርሽራቸውን ሳይቀር አቋርጠው ወደ ጦር ግምባር እየዘመቱ ባለበት በዚህ ሰዓት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ ግን አሁንም እየተዝናና ነው በሚል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ጉዳዩ በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ልጃቸው ዬር ኔታንያሁ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በሚያጋራቸው መረጃዎች በተደጋጋሚ ለትችት ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ልጃቸው በማህበራዊ ትስር ገጾች ላይ ስለሚያጋራቸው መረጃዎች ጥንቃቄ እንዲወስድ አስጠንቅቀውት እንደነበር ዴይሊ ሜይል ዘግቧል፡፡