እስራኤል የጋዛን ጥቃት 'ለአፍታ እንድታቆም' በአጋሮቿ የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች
በጋዛ እየተደበደቡ ባሉ ሚሊዮኖች ዓለም አቀፋዊ ጭንቀቱ እየጨመረ ነው
እስራኤል በዚህ ጊዜ ሰብዓዊ እረፍትን ወይም የተኩስ አቁምን እቃወማለሁ ብላለች
እስራኤል በምዕራቡ ዓለም የቅርብ አጋሮቿ "የሰብዓዊ እረፍት" ወይም የቦምብ ጥቃቱን በጊዜያዊነት እንድታቆም የቀረበላትን ጥሪ ውድቅ አድርጋለች።
በከባድ የአየር ድብደባ ተሰንገው የተያዙ 2.3 ሚሊዮን ሰዎች ሁኔታ ላይ ዓለም አቀፋዊ ጭንቀቱ እየጨመረ ነው።
በዚህ ሳምንት ታላላቅ ኃያላን መንግስታት እስራኤል ፋታ እንድትሰጥ እና ሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ እንዲሁም የእስራኤላውያን ታጋቾች እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል።
እስራኤል ጋዛ ላይ እየወሰደች ባለችው ከባድ ጥቃት በእስራኤላዊያን መካከልም ልዩነት የተፈጠረ ሲሆን፤ የቅርብ አጋሮቿ አሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረት፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የቡድን ሰባት አባላት አፍታ እንድትወስድ ተጠይቃለች።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሊዮር ሃይት "እስራኤል በዚህ ጊዜ ሰብዓዊ እረፍትን ወይም የተኩስ አቁምን ትቃወማለች" ብለዋል።
አንድ ከፍተኛ የእስራኤል ባለስልጣን በበኩላቸው ውጊያው እንዲቆም የቀረበውን ጥሪ ደካማ እይታ ላይ የተመሰረተ በሚል አጣጥለውታል።
በኒውዮርክ እና በብራስልስ የሚገኘው የተመድ ዋና ጽህፈት ቤት ለቀናት የጠነከረ የዲፕሎማሲ ስራን ተከትሎ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ይደረግ በሚሉ እና የእስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት በሚሉ መካከል ለማስታረቅ ሞክሯል።
እስራኤል ከሦስት ሳምንት በፊት በሀማስ በደረሰባት ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ አንድ ሽህ 400 ሰዎችን ተገድለዋል። ከ200 በላይ ሰዎች ደግሞ ታግተው በሀማስ እንደተወሰዱ ተናግራለች።