እስራኤል በግብጿ ታባ ከተማ ለደረሰው ፍንዳታ የሆውዚ ታጣቂዎች ኃላፊነት ይወስዳሉ አለች
እስራኤል የፍንዳታውን መንሰኤ እንደምታጣራ በዛሬው እለት ጠዋት ገልጻ ነበር
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "እስራኤልን ለመጉዳት ያለመው አሸባሪ ድርጅት በግብጽ የጸጥታ አካላት ላይ ያደረሰውን ጉዳት አወግዛለሁ" ብሏል
እስራኤል በግብጿ ታባ ከተማ ለደረሰው ፍንዳታ የሆውዚ ታጣቂዎች ኃላፊነት ይወስዳሉ አለች።
እስራኤል በግብጿ ታባ ከተማ ሆስፒታል በመውደቅ ስድስት ሰዎችን ላቆሰለው የሚሳይል ፍንዳታ የሆውዚ ታጣቂዎች ኃላፊነቱን ይወስዳሉ ስትል በይፋ አስታውቃለች።
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ"እስራኤልን ለመጉዳት ያለመው አሸባሪ ድርጅት በግብጽ የጸጥታ አካላት ላይ ያደረሰውን ጉዳት አወግዛለሁ" ብሏል።
"ሀውዚዎች ሄዝቦላን፣ እስላማዊ ጅሃድን እና ሀማስን የያዙ የኢራን ወኪሎች ናቸው" ብሏል መግለጫው።
እስራኤል የፍንዳታውን መንሰኤ እንደምታጣራ በዛሬው እለት ጠዋት ገልጻ ነበር።
የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤሌ ሀጋሪ እንዳስታወቁት "ዛሬ ጠዋት ከቀይ ባህር ቀጣና የመጣ የአየር ጥቃት ተከላክለናል። እስራኤል በቀይ ባህር ቀጣና ያሉ ስጋቶችኝ ለመከላከል ከግብጽና ከአሜሪካ ጋር ትሰራለች"።
ሀጋሪ የእስራኤልን ደህንነት ለማስጠበቅ ሁሉንም ነገር እናደርጋለን ብለዋል።
ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ጥቃት ከፈጸመበት ከባለፈው ጥቅምት መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ እስራኤል የሀማስ ይዞታ የሆነችውን ጋዛን በአየር በመደብደብ ላይ ነች። እስራኤል ከአየር ጥቃቱ በተጨማሪ ሲጠበቅ የነበረው በእግረኛ ጦር የማጥቃት ዘመቻ ጀምራዋለች።
ሀማስ በበኩሉ እስራኤል ለምታደርገው የመሬት ወረራ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
አለምአቀፍ የመብት ተቋማት በጋዛ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ ቀውስ ስለተከሰተ ተጎጅዎችን ለመድረስ ተፋላሚ ኃይሎች ግጭቱን እንዲያቆሙ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።