የተመድ ልዩ አስቸኳይ ስብሰባ በጋዛ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዛሬው እለት ባካሄደው ልዩ እና አስቸኳይ ጉባዔው ላይ በጆርዳን በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
በጆርዳን የቀረበው የውሳኔ ሀሳቡ በጋዛ የሚደረገው ጦርነት የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቅ ነው።
በዚህም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባካሄደው ልዩ እና አስቸኳይ ጉባዔው በጋዛ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም በጆርዳን የቀረበው የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ጥሪ 120 ድጋፍ፣ 14 ተቃውሞ እና 45 ድምጸ ተአቅቦ ጸድቋል።
በጉባዔው ላይ የተሳተፈችው ኢትዮጵያ በጋዛ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንድደረግ በሚጠየቀው ውሳኔ ላይ ድምጸ ተዓቅቦ አድርጋለች።
ተመድ አስቸኳይ ልዩ እና አስቸኳይ ጉባዔውን እያደረገ ባለበት ሰዓት እስራኤል በምድር ጦር በጋዛ የምታደርገውን ዘመቻ አስፋፍታ መቀጠሏን አስታውቃለች።
የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዛሬ ማምሻውን በሰጠት መግለጫ፤ የምድር ኃይላችን በጋዛ የሚያደርገውን ዘመቻ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ አስፋፍቶ ያካሂዳል ብለዋል።
የጋዛ ነዋሪዎች ከሰሜን የከተማዋ አካባቢ ወደ ደቡብ ለቀው እንዲወጡም ጦሩ አሳስቧል።
ሃማስ በበኩሉ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ፤ እስራኤል ግንኙነት በማቋረጥ ከአየር፣ ከምድር እና ከባሀር የምታደርገውን ጥቃት አጠናክራለች ሲል ከሷል።
ሃማስም እስራኤል በጋዛ ለምታካሂደው የምድር ወረራ ተገቢውን ምለሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።