እስራኤል የአፍሪካ ህብረት አልጀሪያና እና ደቡብ አፍሪካ በፈጠሩት ጫና ከዚህ ቀደም ለእስራኤል በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንድትገኝ የላከውን ግብዣ ሰርዟል ብላለች
በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የእስራኤል ልዑካን እንዳይሳፉ መደረጋቸውን ቴል አቪቭ ተቀባይነት የለውም ብላለች።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የእስራኤል ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የመክፈቻ ስነስርዓት አልተሳተፈም።
እስራኤል ይህን ያደረጉት ደቡብ አፍሪካ እና አልጄሪያ ናቸው ስትል ወቅሳለች።
ሚኒስቴሩ በመግለጫው ይህ ክስተት እጅግ አደገኛ ነው ብሏል።
እስራኤል የአፍሪካ ህብረት እንደ አልጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ባሉ ሀገራት እጅ ወደ “ታጋችነት” መቀየሩ አሳዛኝ ነው ብላለች።
የእስራኤሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "የአፍሪካ ሀገራት ይህን ህብረቱን በመጀመሪያ ደረጃ እና መላውን የአፍሪካ አህጉር የሚነካ ባህሪ እንዲጋፈጡ" ጠይቋል።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊዮር ሃያት በሰጡት መግለጫ “እስራኤላውያን የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር የነበሩትን አምባሳደር ሳሮን ገብስን ከአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የመባረሯን ጉዳይ በጥሞና እያጤነች ነው፣ ምንም እንኳን በጉባኤው ላይ የእውቅና ታዛቢ ሆና እና እርሷ ብትሆንም የመግቢያ ካርዶች የያዘች ብትሆንም ተከልክላለች።"
የእስራኤል የህዝብ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን "የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በአልጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ በፈጠሩት ጫና ከዚህ ቀደም ለእስራኤል በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንድትገኝ የላከውን ግብዣ ሰርዟል" ብሏል።
የእስራኤል ታይምስ ጋዜጣ በጉባኤው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የደህንነት አባላት ወደ እስራኤል ልዑካን ቀርበው እንዲወጡ መጠየቃቸውን አመልክቷል። .