እስራኤል ከሩሲያ ጋር ባላት ውስብስብ ግንኙነት በጦርነቱ የያዘችውን አቋም ልትቀይር ትችላለች ተብሏል
ሩሲያ እስራኤል ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳታቀርብ አስጠነቀቀች
ሩሲያ እስራኤል ለኪየቭ የጦር መሳሪያ በማቅረብ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ እንዳትሳተፍ አስጠንቅቃለች።
ሞስኮ ይህ ዓይነቱ እርምጃ ቀውሱን ወደ መባባስ ያመራል ብላለች።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል-አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ “የጦር መሣሪያ የሚያቀርቡ ሀገራት በሙሉ ለሩሲያ ጦር ኃይሎች ኢላማ እንደሆኑ አድርገን ነው እንቆጥረዋለን” ብለዋል።
"ማንኛውም የጦር መሳሪያ አቅርቦት ሙከራዎች ወደ ቀውስ ያመራሉ። እናም ሁሉም ሰው ይህን ማወቅ አለበት" ብለዋል።
የዛካሮቫ አስተያየት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ለዩክሬን ከሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እያሰቡ መሆኑን ከተናገሩ ከአንድ ቀን በኋላ የመጣ ነው ።
ይህ እርምጃ እስራኤል በጦርነቱ ላይ የነበራትን የቀድሞ አቋም የቀየረ መሆኑን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል።
ኔታንያሁ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት ሀገራቸው ለዩክሬን ከሰብዓዊ ዕርዳታ በተጨማሪ “ሌሎች ዕርዳታዎችን” ለመስጠት እያጤነች ነው።
እስራኤል ለዩክሬን የመከላከያ ዕርዳታን ለመስጠት ቃል አልገባችም ተብሏል። ሆኖም ሀገሪቱ ከሩሲያ ጋር ባላት ውስብስብ ግንኙነትና ሞስኮ ከኢራን ጋር ያላት ግንኙነት እያደገ በመምጣቱ እየሩሳሌም አቋሟን ልትቀይር ትችላለች ተብሏል።
ባለፈው ሳምንት የእስራኤል የመከላከያ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ለፎክስ ኒውስ "የጸጥታ ጥበቃ ፖሊሲ አልተለወጠም" ብለዋል።
እስራኤል ከአሜሪካ ሚሳይሎችን ለዩክሬን እንድትልክ ቀረበ የተባለውን ጥያቄ ውድቅ አድርጋለች።