የእስራኤል ጦር የደቡብ ኮማንድ አዛዥ ጀነራል ዮራን ፍንቅልማን የእግረኛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ከባድ ውጊያ መካሄዱን ተናግረዋል።
እስራኤል ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ከባድ የተባለ ውጊያ ማካሄዷን ገለጸች።
በደቡባዊ ጋዛ ያለችውን ትልቋን ከተማ የደበደበችው እስራኤል ሀማስን ለማጥፋት በጋዛ የእግረኛ ጦር ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ ከባድ ውጊያ ማድረጓን መሆኗን ሮይተርስ ዘግቧል።
የእስራኤል ዋነኛ አጋር የሆነችው አሜሪካ፣ እስራኤል የንጹሃን ፍልስጤማውያንን ጉዳት እንድትቀንስ ጫና በማሳደር ላይ ነች።
በጦር ጄት የታገዙት የእስራኤል ወታደሮች በትናንትናው እለት በደቡባዊ ጋዛ የምትገኘውን ካን ዮኒስ መክበብ ችለዋል።
የሀማስ አል ቃሳም ብርጌድ ተዋጊዎቹ ከእስራኤል ጋር ከባድ ውጊያ እያካሄዱ ነው ብሏል።
የእስራኤል ጦር የደቡብ ኮማንድ አዛዥ ጀነራል ዮራን ፍንቅልማን ባወጡት መግለጫ "የእግረኛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ከባድ ውጊያ ላይ ነን" ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ ውጊያ በኳታር አደራዳሪነት ተደርሶ የነበረው ጦርነቱን ጋብ የማድረግ ስምምነት ከተጣሰ በኋላም እጅግ ከባድ የሚባል ነው።
የእስራኤል ወታደሮች በሰሜን ጋዛ ትልቁ የጃባልያ የስደተኞች ካምፕ እና ከጋዛ ከተማ ቀጥሎ ባለው የሀማስ ይዞታ ላይ ውጊያ እያካሄዱ ናቸው።
በውጊያው አልቀሳም ብርጌድ ስምንት የእስራኤል ወታደሮችን መግደሉን እና 24 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ማውደሙን ገልጿል።
የእስራኤል ጦር ግን በትናንትናው ውጊያ የተገደሉት ሁለት ወታደሮች መሆናቸውን በድረገጹ ዘርዝሯል። ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በአጠቃላይ የሞቱት የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 83 ደርሷል።
እስራእል እየወሰደች ባለው የአየር እና የመሬት ጥቃት 16ሺ ገደማ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ሀማስን ለማጥፋት እየተንቀሳቀሰች ያለችው እስራኤል ጦርነቱን ለማቆም ፈቃደኛ አልሆነችም።