መስክ እና እስራኤል ስታርሊንክ በጋዛ ኢንተርኔት እንዲያቀርብ በመርህ ደረጃ ተስማሙ
ስታርሊንክ በጋዛ አገልግሎት መስጠት የሚችለው እስራኤል ፍቃድ ስትሰጠው ብቻ ይሆናል ተብሏል
አይሁዳውያን በነጮች ላይ ጥላቻ አላቸው ብሎ በኤክስ ላይ የጻፈን ግለሰብ ሀሳብ በመደገፉ ምክንያት መስክ ከፍተኛ ትችት ቀርቦበት ነበር
መስክ እና እስራኤል ስታርሊንክ በጋዛ ኢንተርኔት እንዲያቀርብ በመርህ ደረጃ ተስማሙ።
እስራኤል የኤሎን መስክ ስፔስ ኤክስ ሳተላይት ኩባንያ ስታርሊንክ በጋዛ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሰጥ መስማማቷን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
ነገረግን ስታርሊንክ በጋዛ አገልግሎት መስጠት የሚችለው እስራኤል ፍቃድ ስትሰጠው ብቻ ይሆናል።
ባለፈው ወር መስክ በጋዛ ለሚገኙ አለምአቀፍ እውቅና ላላቸው ድርጅቶች በስታርሊንክ በኩል የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት ሀሳብ ማቅረቡ ይታወሳል።
መስክ ይህን አዲስ እቅድ ይዞ የመጣው የእራኤል የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ሽሎሞ ካርሂ የመጀመሪያውን እቅዱን ስለተቃወሙት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።
መስክ በዛሬው እለት ቴልአቪቭ በመግባት ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና ከእስራኤሉ ፕሬዝደንት ኢሳቅ ሄርዞግ ጋር መገናኘቱን የእስራኤል ሚዲያዎች ዘግበዋል።
የሄርዞግ ቢሮ ከስብሰባው በፊት ጸረ-ሴማዊነትን በኦንላይን በመዋጋት ጉዳይ ትኩረት እንደሚያስፈልግ ገልጿል።
ይህ የተባለው መስክ የጸረ-ሴማዊነት ሀሳብን ደግፏል የሚል ተቃውም ከቀረበበት በኋላ ነው።
አይሁዳውያን በነጮች ላይ ጥላቻ አላቸው ብሎ በኤክስ ላይ የጻፈን ግለሰብ ሀሳብ በመደገፉ ምክንያት መስክ ከፍተኛ ትችት ቀርቦበት ነበር።
ኤሎን መስክ ሩሲያ የዩክሬንን የኢንተርኔት መሰረተልማቶች ባጠፋችበት ወቅት በስታርሊንክ በኩል አገልግሎት ሰጥቷል።