እስራኤል ከጦርነቱ በኋላ በጋዛ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ ቀጣና እንደምትፈልግ ተናገረች
ተኩስ አቁሙን በመጣስ እስራኤል እና ሀማስ እርስበእርሳቸው እየተካሰሱ ናቸው
እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለው ወታደራዊ ዘመቻ የሚጠናቀቀው ሀማስን ከምድረገጽ ስታጠፋ እንደሆነ በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወሳል
እስራኤል የሚጠናቀውቀተጠናቀቀ በኋላ ሌላ ጥቃት እንዳይደርስባት በጋዛ በኩል ነጻ ቀጣና ወይም 'በፈር ዞን' እንደምትፈልግ ለበርካታ አረብ ሀገራት አሳውቃለች።
ሮይተርስ የግብጽ እና የቀጣናውን ምንጮች ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ እስራኤል ለጎረቤቶቿ ግብጽ እና ጆርዳን እቅዷን ተናግራለች።
ከሁለቱ ሀገራት በተጨማሪ በ2020 ግንኙነቷን ከእስራኤል ጋር ላደሰችው አረብ ኢምሬትስም እቅዱን ማሳወቋን ዘገባው ጠቅሷል።
ከእስራኤል ጋር መደበኛ ግንኙነት የሌላት እና በአሜሪካ አደራዳሪነት ከእስራኤል ጋር ስታደርግ የነበረውን ግንኙነት የማደስ ሂደት በጋዞ ጦርነት ምክንያት ያቋረጠችው ሳኡዲ አረቢያ እቅዱ ተነግሯታል።
አረብ ያልሆነችው እና በሀማስ-እስራኤል ጦርነት፣ እስራኤልን በጽኑ የተቸችው ቱርክም መረጃው ደርሷታል።
ይህ የእስራኤል ፍላጎት በኳታር አደራዳሪነት ተደርሶ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሶ የተቀሰቀሰው ጦርነት በቀላሉ እንደማይቆም የሚያሳይ ነው ተብሏል።
እስራኤል ከጦርነት በኋላ ያለውን ሁኔታ ለማመቻቸት ከአረብ አደራዳሪዎች ማለትም ከግብጹ እና ኳታር ባሻገር ልትፈልግ ትችላለች።
በሀማስ የታገቱ እስራኤላውያን እና በእስራኤል ታስረው የነበሩ ፍልስጤማውያን እንዲለቀቁ ያስቻለው ለሁለት ጊዜ የተራዘመው ተኩስ አቁም ስምምነት በትናንትናው እለት ተጥሷል።
ተኩስ አቁሙ መጣሱን ከገለጸች በኋላ እስራኤል በጋዛ ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት በርካታ ፍልስጤማውያን የመቁሰል እና የሞት አደጋ እንደደረሰባቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
ተኩስ አቁሙን በመጣስ እስራኤል እና ሀማስ እርስበእርሳቸው እየተካሰሱ ናቸው።
እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለው ወታደራዊ ዘመቻ የሚጠናቀው ሀማስን ከምድረገጽ ስታጠፋ እንደሆነ በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወሳል።