እስራኤል ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ ሐማስ መሪ የነበሩት እስማኤል ሀኒየህን በኢራን መግደሏ ይታወሳል
እስራኤል የሐማሱን መሪ ያህያ ሲንዋር መግደሏን ገለጸች፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት ሐማስ በእስራኤል ምድር ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ነበር በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የተቀሰቀሰው፡፡
1 ሺህ 200 ሰዎች በሐማስ ጥቃት ተገድለውብኛል ያለችው እስራኤል ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የድርጅቱ የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎችን ገድላለች።
የድርጅቱ የፖለቲካ ክንፍ መሪ የነበሩት እስማኤል ሀኒየህ በኢራን መዲና ቴህራን በእስራኤል ጥቃት ከተገደሉ በኋላ ያህያ ሲንዋር ተመርጠው ነበር፡፡
ያህያ ሲንዋር ሐማስ በእስራኤል ላይ የተፈጸመውን ያልተጠበቀ ጥቃት ከሀሳብ ማመንጨት ጀምሮ ጥቃቱን እንደመሩ ይታመናል።
የእስራኤል ብዙሃን መገናኛዎች እንደዘገቡት ከሆነ ያህያ ሲንዋር በጋዛ ጀባሊያ በተባለው አካባቢ በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል፡፡
ሂዝቦላህ በእስራኤል የትኛውንም ኢላማ መምታት እንደሚችል ዛተ
ይሁንና እስራኤል የያህያ ሲንዋርን መገደል ለማረጋገጥ እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የሃማሱ መሪ ያህያ ሲንዋር መገደሉን የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጧል።
የእስራኤል ጦር በበኩሉ፤ የሃማስ መሪ ያህያስ ሲንዋር በትናትናው እለት በደቡባዊ ጋዛ ውስጥ በተደረገ ኦፕሬሽን መገደላቸውን አስታውቋል።
ሒብሪው ቋንቋ አቀላጥፎ መናገሩ ስለ እስራኤል ባህል በሚገባ እንዲያውቅ ረድቶታል ተብሏል።
ዝምተኛ ነው የሚባለው ሲንዋር የሐማስ ታጣቂዎች በጋዛ እስራኤልን ለመመከት የዋሻ ውስጥ ውጊያዎችን እየመራ እንደነበርም ተገልጿል።