ሂዝቦላህ በእስራኤል የትኛውንም ኢላማ መምታት እንደሚችል ዛተ
እስራኤል በበኩሏ ሂዝቦላህ ባለበት ቦታ ሁሉ እንደምትመታ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ መናገራቸው ይታወሳል
እስራኤል በሊባኖስ ቦታ ሳትመርጥ እየደበደበች በመሆኑ ሂዝቦላህም ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርግ ዝቷል
ሂዝቦላህ በእስራኤል የትኛውንም ኢላማ መምታት እንደሚችል ዛተ፡፡
አንድ ዓመት ያለፈው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ የቀጠለ ሲሆንእስራኤል በሊባኖስ የአየር እና የመሬት ላይ ጥቃቷን ቀጥላለች፡፡
የአጸፋ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሚናገረው ሂዝቦላህ በበኩሉ እስራኤል በሊባኖስ በሁሉም ቦታ ጥቃት እያደረሰች መሆኗን ገልጿል፡፡
የቡድኑ ምክትል ሀላፊ ናይም ቃሲም እንዳሉት ሂዝቦላህ በእስራአል የትኛውም ቦታ ላይ ጥቃት የመሰንዘር አቅም እንዳለው ተናግረዋል፡፡
እስራኤል በሊባኖስ ማንኛውም ቦታዎች ለይ ጥቃት እየሰነዘረች ነው ያሉት ምክትል አዛዡ ሂዝቦላህም በተመሳሳይ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል፡፡
እንደ ቃሲም ገለጻ ከሆነ ለጊዜው ሂዝቦላህ የእስራኤልን ወታደራዊ ተቋማትን ብቻ ማጥቀቱን ይቀጥላል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ቃሲም አክለውም ጦርነቱን ማስቆሚያ ብጨኛው መንገድ የተኩስ አቁም ነው ያሉ ሲሆን ይህን የምንለው ሽንፈትን በመፍራት አይደለም ብለዋል፡፡
እስራኤል የኢራን ኑክሌር ማብለያ እና ሌሎች ኢሊማዎችን ለመምታት የያዘችውን አቅድ መተዋ ተገለጸ
እስራኤል በሂዝቦላህ ስለተሰጠው አስተያየት እስካሁን በይፋ ምላሽ ያልሰጠች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ቤሩትን ጨምሮ ሂዝቦላህ ባለበት ሁሉ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል፡፡
80 ሺህ ገደማ እስራኤላዊን ከሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ ከሚኖሩበት ቤታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን በሊባኖስ በኩል ደግሞ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን በላይ ሆኗል፡፡
ሂዝቦላህ ባሳለፍነው እሁድ በእስራኤል ወታደሮች ላይ በሰነዘረው ጥቃት አራት ወታደሮች ሲገደሉ ከ60 በላይ መቁሰላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡