እስራኤል የሩሲያ እና ቻይና ጸረ ታንክ መሳሪያዎች በሊባኖስ ማግኘቷን ገለጸች
በጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት በደቡባዊ ሊባኖስ የጦር መሳሪያ የመያዝ ስልጣን ያለው የሀገሪቱ ብሔራዊ ጦር ብቻ ነበር
ከተገኙት ጦር መሳሪያዎች ውስጥ አብዛኞቹ ዘመናዊ የሩሲያ ጦር መሳሪያዎች ናቸው ተብሏል
እስራኤል የሩሲያ እና ቻይና ጸረ ታንክ መሳሪያዎች በሊባኖስ ማግኘቷን ገለጸች፡፡
አንድ ዓመት ያለፈው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በሰላም ስምምነት ይጠናቀቃል ቢባልም አድማሱን እያሰፋ ይገኛል፡፡
የእስራኤል ጦር ከሐማስ ታጣቂዎች ባለፈ ከሊባኖሱ ሂዝቦላህ ጋር የመሬት እና የአየር ለይ ውጊያዎችን በማድረግ ላይ ነው፡፡
የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ እያደረገው ያለው ጦርነት ከጋዛው ጋር ሲነጻጸር ከባድ እና ጉዳቱም እንዳየለበት ተገልጿል፡፡
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ለኤኤፍፒ እንዳሉት በደቡባዊ ሊባኖስ የሩሲያ እና ቻይና ስሪት የሆኑ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተያየት ከሆነ ሂዝቦላህ በቆፈራቸው የመሬት ውስጥ ዋሻዎች ውስጥ የቻይና እና ሩሲያ ስሪት የሆኑ ጸረ ታንክ መሳሪያዎች ተገኝተዋል፡፡
ሂዝቦላህ በእስራኤል የትኛውንም ኢላማ መምታት እንደሚችል ዛተ
የመንግስታቱ ድርጅት ጸጥታው ምክር ቤት በፈረንጆቹ 2006 ባሳለፈው ውሳኔ በደቡባዊ ሊባኖስ ከሊባኖስ ብሔራዊ ጦር ውጪ የጦር መሳሪያ መያዝ አልተፈቀደም ነበር ተብሏል፡፡
ሩሲያ እና ቻይና እስካሁን በሂዝቦላህ እጅ ተገኝተዋ ስለ ተባሉት የጦር መሳሪያዎች ጉዳይ ምላሽ አልሰጡም፡፡
በእስራኤል እና ሂዝቦላህ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን እስራኤል ጦርነቱን ለማቆም ከሂዝቦላህ የቀረበላትን የተኩስ አቁም ስምምነት ውድቅ አድርጋለች፡፡