የወሊድ መከላከያ ህክምና የወሰደው አባወራ ድጋሚ አባት መሆኑን ተከትሎ ክስ መሰረተ
የአራት ልጆች አባት የሆነው ሰው እርግዝና እንዳይፈጠር የሚከላከል ህክምና ቢያደርግም ሳይፈልግ አምስተኛ ልጅ አባት ለመሆን ተገዷል
የሕክምና ስህተት የሰራው ተቋም ልጄ 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ የማሳደጊያ ይከፈለኝ ሲል ክስ መስርቷል
የወሊድ መከላከያ ህክምና የወሰደው አባወራ ድጋሚ አባት መሆኑን ተከትሎ ክስ መሰረተ፡፡
ማክሲም የተሰኘው ሩሲያዊ የ45 ዓመት አባወራ ሲሆን የአራት ልጆች አባትም ነው፡፡ የኢኮኖሚ እና ሌሎች አቅሙን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከባለቤቱ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ተጨማሪ ልጆችን ላለመውለድ ይወስናሉ፡፡
ዘላቂ የወሊድ መከላከያ ለመውሰድ የተስማሙት እነዚህ ወላጆች አባትየው እርግዝና እንዲፈጠር የሚያደርገውን ወይም የዘር ፍሬ ቱቦ በማስቆረጥ ወይም በእንግሊዘኛው ቫስክቶሚ የተሰኘውን ህክምና ያደርጋል፡፡
በዘር ፍሬ ቱቦው ላይ ባደረገው የቀዶ ህክምና አማካኝነት ልጅ መውለድ እንደማይችል የተነገረው ይህ ሰውም ባለቤቱ አምስተኛ ልጅ እርጉዝ መሆኗን ትነግረዋለች፡፡
በውጤቱ የተጠራጠረው ይህ ሰውም ድጋሚ ባደረገው ምርመራ አምስተኛ ልጅ አባት ለመሆን የተገደደ ሲሆን ህክምናውን ባደረገለት ክሊኒክ ላይ ክስ መስርቷል፡፡
ቀዶ ህክምናውን ያደረገው ክሊኒክም የተፈጠረውን ነገር ማመን ባለመቻሉ በግለሰቡ ላይ ባደረገው ድጋሚ ምርመራ አሁንም ማስረገዝ እንደሚችል ያረጋግጣል፡፡
ክስ የተመሰረተበት ክሊኒክ ከደንበኛው ለቀዶ ህክምና የተቀበለውን ክፍያ መመለስ እንደሚችል ቢናገርም ግለሰቡ ከዚህ ያለፈ ካሳ እንደሚፈልግ ተናግሯል ተብሏል፡፡
ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ የሆነው አድኖሲን ምንድን ነው?
ያለ ፍላጎቱ የአምስተኛ ልጅ አባት የሆነው ግለሰብ እኔ ህክምናውን ያደረኩት ኢኮኖሚዬን እና የማሳደግ አቅሜን አይቶ እንደነበር እንዲሁም ክሊኒኩ በሰራው ስህተት ምክንያት ለተጨማሪ ጫናዎች መዳረጉን ተናግሯል፡፡
ግለሰቡ ለደረሱበት ጨናዎች ካሳ እንደሚፈልግ ቢናገርም ክሊኒኩ ግን እኔ የሰራሁት ስህተት የለም ነገር ግን ግለሰቡ በተዓምር ነው አምስተኛ ልጅ ሊወልድ የቻለው በሚል ክርክሩ እንደቀጠለ ይገኛል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ከዓመታት በፊት በአሜሪካ ኮሎምቢያ ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞ በህክምና ስህተት ምክንያት ለተወለደው ልጅ ህክምናውን ያደረገው ሐኪም ልጁ 18 ዓመት እስከሚሞላው ድረስ ድጋፍ እንዲያደርግ በፍርድ ቤት ተወስኖበት ነበር፡፡