እስራኤል የሱዳን አየር ክልል መጠቀም ጀመረች
እ.ኤ.አ በ1967 የአረብ ሀገራት ከእስራኤል ጋር ያለመገናኘት ማእቀብ ከጣሉ በኋላ ይህ በረራ የመጀመሪያ ነው
የእስራኤል የአየር ክልል ክፍት የሆነው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታኒያሁ ከአልቡርሀን ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ ነው
የእስራኤል የአየር ክልል ክፍት የሆነው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታኒያሁ ከአልቡርሀን ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ ነው
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኒታኒያሁ በየካቲት ወር መጀመሪያ ሳምንት ከሱዳን ሉአላዊ ምክርቤት ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልቡርሀን ጋር ከተገናኙ በኋላ ለረጅም ጊዜ ለእስራኤል ዝግ የነበረው የሱዳን የአየር ክልል ክፍት ሆኗል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታኒያሁ የእስራኤል የመንገደኞች አውሮፕላኖች በሱዳን የአየር ክልል መብረር ጀምረዋል ብለዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1967 የአረብ ሀገራት ከእስራኤል ጋር ያለመገናኘት ማእቀብ ከጣሉ በኋላ ይህ በረራ የመጀመሪያ ነው፡፡
የሱዳን ሉአላዊ ምክርቤት ፕሬዘዳንት አልቡርሀን ከጠቅላይ ሚኒስትር ኒታኒሁ ጋር ከተገናኙ ከሁለት ቀን በኋላ ካርቱም የእስራኤል አውሮፕላኖች በሱዳን የአየር ክልል እንዲበሩ የመጀመሪያ ደረጃ ፍቃድ ተሰጥቷቸው ነበር፡፤
“አሁን ላይ በፍጥነት ግንኙነታችንን የምንናዳብርበት መንገድ ላይ እየተወያየን ነው፡፡ የመጀመሪያው የእስራኤል አውሮፕላን በትናንትና እለት በሱዳን የአየር ክልል መብረር ችሏል”በማለት ኒታኒያሁ ለአሜሪካ የጀዊሽ መሪዎች ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩ ምንያህል የፍልስጤማውያንን እንደሚያስቆጣ ያወቀችው ሱዳን ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ማደሷን መናገር አልደፈረችም፡፡
ቀደም ባለው ጊዜ ኢራን ሱዳንን እንደመተላለፊያ መንገድ በመጠቀም የጦር መሳሪያ ወደ ጋዛ ስርጥ ታስገባለች በሚል እስራኤል ሱዳንን እንደ ደህንነት ስጋት ትጠረጥራት ነበር፡፡ እ.ኤ.አ.በ2009 እስራኤል በሱዳን ውስጥ የወታደራዊ መኪና መደብደባን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል፡፡