2.3 ሚሊየን ፍሊስጤማውያን ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
በእሰራኤልና በፊልስጤሙ ሃማስ መካከል የተቀሰቀሰው ጠሮርት 83ኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን፤ አሁንም እንደቀጠለ ነው።
ሃማስ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሱን ቀጥሏል፤ እስራኤልም ከአየር ድብደባ በተጨማሪ እግረኛ ጦሯን ወደ ጋዛ በማስገባት ከሃማስ ጋር እየተዋጋች ትገኛለች።
በትናንትናው እለት በተደረገ ውጊያ ሶስት ወታደሮች በጋዛ እንደተገደሉበት የእስራኤል ጦር አስታውቋል።
ይህንን ተከትሎም እስራኤል በጋዛ በምድር ጦር ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ የሞቱ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 167 መድረሱንም የእስራኤል ጦር መረጃ ያመለክታል።
ከሞቱ ወታደሮች በተጨማሪም 898 የእስራኤል ወታደሮች እንደቆሰሉም ነው ተገለጸው።
በተያያዘ በጋዛ የሞቱ ፍሊስጤማውያን ቁጥር 21 ሺህ 110 መድረሱን እና 55 ሺህ 223 ሰዎች መቁሰላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በተጨማሪም ከ7 ሺህ በላይ ፍሊስጤማውያን እስካሁብ የት እንደገቡ አይታወቅን የተባ፤ ሲሆን፤ 2.3 ሚሊየን ፍሊስጤማውያን ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።
በዌስት ባንክም የእስራኤል ጦር በፈጸማቸው ጥቃቶች 313 ፍሊስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን፤ 3 ሺህ 450 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
በእስራኤል በኩል ሃማስ ጥር 7 በፈጸመው ጥቃት የሞቱ እስራኤላውያን ቁጥር 1 ሺህ 139 ላይ ይገኛል።