የግብጽ ባለስልጣናት የእቅዱን ዝርዝሩ ከኳታር፣ ከእስራኤል፣ ከሀማስ፣ ከአሜሪካ እና ከአውሮፖ መንግስታ ጋር ውይይት እንደተደረገበት ተናግረዋል
ግብጽ ጦርነቱን ያስቆማል ያለችውን እቅድ አቅርባለች።
እስራኤል እና ሀማስ በትናንተናው እለት ግብጽ ጦርነቱን ያስቆማል ያለችውን እቅድ እያቅማሙ መቀበላቸውን ኤፓ ዘግቧል።
- ታግተው የነበሩ እስራኤላውያን ሞተው መገኘታቸውን የእስራኤል ጦር አስታወቀ
- የጋዛው ጦርነት ባደበዘዘው የግብጽ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አልሲሲ አሸነፉ
ነገርግን የረጅም ጊዜ ተቀናቃኞቹ እቅዱን አለመቃወማቸው፣አውዳሚ የሆነውን የእስራኤል የጋዛ ጥቃት ለማቆም አዲስ የዲፕሎማሲ ንግግር ለመክፈት ሊረዳ ይችላል ተብሏል።
እንደዘገባው ከሆነ ግብጽ ታጋቾች እንዲለቀቁ እና ጋዛን እና ዌስትባንክን የሚያስተዳድር የፍልስጤም መንግስት የባለሙያዎች ቡድን እንዲቋቋም ሀሳብ አቅርባለች።
የግብጽ ባለስልጣናት የእቅዱን ዝርዝሩ ከኳታር፣ ከእስራኤል፣ ከሀማስ፣ ከአሜሪካ እና ከአውሮፖ መንግስታ ጋር ውይይት እንደተደረገበት ተናግረዋል።
ግብጽ እና ኳታር ተቀናቃኞቹን እስራኤልን እና ሀማስን የሚያደራድሩ ሲሆኑ አሜሪካ ደግሞ የእስራኤል የቅርብ አጋር እና በቀጠናው ቁል ሚና ያላት ሀገር ነች።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ግብጽ አቅርባዋለች በተባለው ሀሳብ ላይ ቀጥተኛ አስተያየት አልሰጡም።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለልኩድ ፖርቲ አባለት እንደተናገሩት እስራኤል ባለፈው ጥቅምት ወር ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት ያደረሰባትን ሀማስን ለማጥፋት የምታደርገውን ዘመቻ አጠናክራ ትቀጥላለች።
እስራኤል ሀማስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በከፈተችው መጠነሰፊ ጥቃት ከ20ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ከተጀመረ ከ11 ሳምንታትን ያስቆጠረው ጦርነት አሁንም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።