ጦርነቱ ለወራት ሊቆይ እንደሚችል የእስራኤል ጦር አዛዥ ገለጹ
ድንበሯን ጥሶ ጥቃት ያደረሰባትን ሀማስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ያቀደችው እስራኤል ማጥቃቷን አሁንም እንደቀጠለች ነው
የጦሩ አዛዥ ኸርዚ ሀለቪ በትናንትናው እለት ከጋዛ ድንበር ሆነው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ጦርነቱ "ለብዙ ወራት" ሊዘልቅ ይችላል ብለዋል
እስራኤል በሀማስ ላይ የምታካሂደው ጦርነት ለወራት ሊቆይ እንደሚችል የእስራኤል ጦር አዛዥ ገለጹ።
የእስራኤል ጦር አዛዥ እስራኤል በሀማስ ላይ እያካሄደችው ያለው ጦርነት ለወራት ሊቆይ ይችላል ብለዋል።
የጦሩ አዛዥ ኸርዚ ሀለቪ በትናንትናው እለት ከጋዛ ድንበር ሆነው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ጦርነቱ "ለብዙ ወራት" ሊዘልቅ ይችላል ብለዋል።
ሀለቪ "ምትሀታዊ መፍትሄ የለም፤ የሽብር ድርጅትን ለማስወገድ አቋራጭ መንገድ የለም። አማራጩ በቁርጠኝነት እና ያለማቋረጥ መዋጋት ነው" ብለዋል።
"ሳምንትም ይፍጅ ወራት የሀማስን አመራር እንደርስበታለን"
እስራኤል ቀደም ሲል በሰሜን ጋዛ ያሉ ነዋሪዎች የሰላም ቀጣና ነው ወደምትለው የደቡብ ጋዛ እንዲሄዱ አሳስባ ነበር።
ነገር ግን የእስራኤል ጦር የጥቃት አድማሱን ከሰሜን ጋዛ ወደ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጋዛ በማስፋት መጠነ ሰፊ ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛል።
የተመድ የሰብአዊ መብት ቢሮ ባወጣው መግለጫ እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ የሚገኙትን የቡርጂ፣ የኑስሪያት እና የማጋዚ ካምፖችን ኢላማ ያደረገ 50 የአየር ጥቃቶችን አድርሳለች።
ቢሮው እንደገለጸው በሁለቱ የአየር ጥቃት ብቻ 86 ሰዎች ተገድለዋል።
ድንበሯን ጥሶ ጥቃት ያደረሰባትን ሀማስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ያቀደችው እስራኤል ማጥቃቷን አሁንም እንደቀጠለች ነው።
ለጋዛ እርዳታ እንዲገባ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥያቄ ቢቀርብም፣ በእስራኤል እና በአጋሯ ግን ይህን ሀሳብ አይቀበሉም።