እስራኤል በጋዛ አካባቢ በስምንት ቦታዎች ውጊያ እያካሄደች መሆኗን ገለጸች
የእስራኤል ጦር በደቡባዊ እስራኤል በጋዛ አካባቢ በስምንት ቦታዎች ላይ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን የጦሩ ቃል አቀባይ ተናግረዋል
የሌባኖሱ ሄዝቦላ ለፍልስጤም ህዝብ "አጋርነት ለማሳየት" ወደ ሰሜን አስራኤል ሮኬት ማስወንጨፉ ግጭቱ አድማሱን እንዲያሰፋ አደርጎታል
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የእስራኤል ጦር ከሀማስ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ገጥሟል ተብሏል።
የእሴራኤል ጦር ከሀማስ ታጣቂዎች ጋር የተጋጨው ሀማስ በ50 አመታት ውስጥ እጅግ ከባድ የተባለውን ጥቃት ሰንዝሮ 500 ሰዎች እንዲገደሉ ያደረገውን ጥቃት ከከፈተ ከ24 ሰአታት በኋላ ነው።
የሌባኖሱ ሄዝቦላ ለፍልስጤም ህዝብ አጋርነት ለማሳየት ወደ ሰሜን አስራኤል ሮኬት ማስወንጨፉን ገልጿል፣ ይህም ግጭቱ አድማሱን እንዲያሰፋ አደርጎታል።
የእስራኤል ጦር ሌባኖስ ውስጥ በሚገኙ የሄዝቦላ ጣቢያዎች ላይ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ የአጸፋ ምላሽ ሰጥቷል።ነገርግን ስለደረሰው ጉዳት የተባለ ነገር የለም።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን በደቡባዊ እስራኤል በኩል ዘልቆ በመግባት ያደረሰው ጥቃት በአሜሪካ የሚመራውን ቀጠናውን የማረጋጋት ስራ እና የፍልስጤምን ሀገር የመሆን ህልም አደጋ ውስጥ የሚከት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል
ሀማስ ባደረሰው ጥቃት 250 እስራኤላውያንን መግደሉ እና የተወሰኑ ወታደሮችን አግቶ ወደ ጋዛ መውሰዱ ተገልጿል።
እስራኤል በወሰደችው የአጸፋ ምላሽ ከ250 በላይ የጋዛ ነዋሪዎች የተገደሉ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል።
የእስራኤል ጦር በደቡባዊ እስራኤል በጋዛ በስምንት ቦታዎች ላይ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን የጦሩ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ምዕራባውያን ሀገራት ሀማስ አድርሷል ያሉትን ጥቃት አውግዘዋል፤ ከእስራኤል ጎን እንደሚሆኑም ግልጽ አድርገዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አሜሪካ፣ እራኤል የተቃጣበትን የሽብር ጥቃት ለመቀልበስ የምትፈልገው ሁሉ እንዲኖራት ታደርጋለች ብለዋል።
እየተካሄደ ባለው ግጭት ዙሪያ፣ ከእራኤል ጋር የዲፕሎማት ለዲፕሎማት፣ የደህንነት ለደህንነት እና የወታደራዊ ለወታደራዊ ተቋማት ውይይት እየተደረገ መሆኑንም ፕሬዝደንቱ ባይደን ገልጸዋል።