እስራኤል በሶሪያ ግዛት ላይ ወረራ ማካሄዷን አስታወቀች
የእስራኤል ጦር በሶሪያ ግዛት ላይ ወረራ ፈጽሞ በኢራን ኔትዎርክ ውስጥ የተሳተፈ ሶሪያዊ ግለሰብ መያዙን በትናንትናው እለት አስታውቋል
እስራኤል ወቅታዊው ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ወታደሮቿ ሶሪያ ውስጥ ገብተው ዘመቻ ማካሄዳቸውን ስታሳውቅ ይህ የመጀመሪያዋ ነው
እስራኤል በሶሪያ ግዛት ላይ ወረራ ማካሄዷን አስታወቀች።
የእስራኤል ጦር በሶሪያ ግዛት ላይ ወረራ ፈጽሞ በኢራን ኔትዎርክ ውስጥ የተሳተፈ ሶሪያዊ ግለሰብ መያዙን በትናንትናው እለት አስታውቋል።
እስራኤል ወቅታዊው ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ወታደሮቿ ሶሪያ ውስጥ ገብተው ዘመቻ ማካሄዳቸውን ስታሳውቅ ይህ የመጀመሪያዋ ነው።
እስራኤል ባለፈው አንድ አመት የሄዝቦላ አባላትን እና ከኢራን የመጡ ባለስልጣናትን ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት ሶሪያ ውስጥ ስትፈጽም ቆይታለች።ነገርግን ከዚህ በፊት ሶሪያ ውስጥ ገብታ ጠብታ ጥቃት ስለመፈጸሟ ይፋ አላደረገችም።
የእስራኤል ጦር ወረራውን መቼ እንፈጸመው ባይገልጽም፣ "በቅርብ ወራት እየተካሄደ ያለው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ አካል ነው" ብሏል።
ሶሪያ የእስራኤልን መግለጫ በተመለከተ መልስ አልሰጠችም።
ነገርግን የሶሪያ መንግስት ደጋፊ የሆነው ሬዲዮ ጣቢያ የእስራኤል ኃይሎች በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል አንድ ሰው ኢላማ ያደረገ "የእገታ ዘመቻ" ማካሄዳቸውን መዝገቡን ሮይተርስ ዘግቧል።
ባለፉት ስድስት ወራት እስራኤል ሄዝቦላን ለማሽመድመድ ያለመ የተጠናከረ የአየር ድብደባ እና የእግረኛ ጦር ጥቃት እያካሄደች ትገኛለች።ባለፈው ቅዳሜ የእስራኤል የባህር ኃይል ባለስልጣናት የባህር ኃይል አባላት በሰሜን ሊባኖስ ከተማ ወረራ አካሂዶ ከፍተኛ የሄዝቦላ ወኪል ነው ያሉትን ሰው መያዛቸውንና ገልጸዋል።
ጦሩ እንደገለጸው ግለሰቡ አሊ ሶሊማን እንደሚባል ሲሆን የሚኖረው በደቡብ ሶሪያዋ ሳኢዳ ግዛት ነው። ጦሩ አክሎም ግለሰቡ ለበርካታ ወራት በወታደራዊ ቅኝት ውስጥ እንደነበረ እና ኢራን ከሶሪያ ጋር በሚዋሰነው እና በእስራኤል ቁጥጥር ባለው ጎላን ሀይት ውስጥ ያሉ ቦታዎችን እንድታጠቃ ሲያመቻች ነበር ብሏል።
በጦሩ የተለቀቀው ወረራውን የሚያሳየው የቦዲ ካሜራ ቪዲዮ ወታደሮች ግለሰቡን ሲይዙት ያሳያል።
ግለሰቡ ለምርመራ ወደ እስራኤል መምጣቱን ጦሩ ገልጿል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንያማን ኔታንያሁ በትናንትናው እለት እስራኤል ከሊባኖስ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር በጎበኙበት ወቅት ጦራቸው ሄዝቦላ ከኢራን በሚያገኘው የጦር መሳሪያ እንዳያንሰራራ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ብለዋል።
እስራኤል በሊባኖስ እያካሄደች ያለው ጦርነት አላማው ሄዝቦላን ከድንበር አካባቢ ለማራቅ እና ቡድኑ ለአንድ አመት ያህል ወደ እስራኤል ያደረገውን ተኩስ ማስቆም ነው ብላለች።
እስራኤል እስካሁን በሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ከ2500 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። እስራኤል ውስጥ ደግሞ 59 ሰዎች ሄዝቦላ በሚያስወነጭፋቸው ሮኬቶች ተገድለዋል።
ሄዝቦላ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን ማስወንጨፍ የጀመረው ለፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ አጋርነት ለማሳየች ነበር።
እስራኤል ወደ ሄዝቦላህ ትኩረቷን ያደረገችው በጋዛ ለአንድ አመት ያህል ባካሄደችው ጦርነት ከፍተኛ ወድመት ካደረሰች እና የሀማስ ከፍተኛ አመራሮችን ከገደለች በኋላ ነው። በሊባኖስ ባደረሰችው ጥቃትም የኢራን ጠንካራ አጋር የሆነውን ሄዝቦላ መሪ ሀሰን ነስረላህን እና በእርግጠኝነት ይተካዋል የተባለው ሀሽም ሰይፈዲንን ገድላለች።