የእስራኤሏ መዲና ቴልአቪቭ በዓለማችን ለመኖር ውዷ ከተማ ናት ተባለ
የሶርያዋ ዶማስቆ “በዓለማችን ኑሮ ቀላል የሆነባት” ከተማ ሆና ቀጥላለች
በ173 ሀገራት በተካሄደ ዳሰሳ በእስራኤል በቤንዚን ዋጋ ብቻ የ21 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል
አሁን ላይ በዓለማችን ካለው ከባድ የዋጋ ንረት ጋር ተያይዞ፤የእስራኤሏ መዲና ቴልአቪቭ በዓለማችን ካሉ ከተሞች “ለመኖር ከበድ የሆነች ውድ ሀገር ናት” ተባለ፡፡
እስራኤላዊቷ ቴልአቪቭ ባለፈው ዓመት አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ የነበረ ቢሆንም፤ በዚሁ ዓመት ፓሪስና ሲንጋፖርን በመብለጥ ለመጀመርያ ገዜ አንደኛ ደረጃ እንደያዘችም ነው የኢኮኖሚስት ኢንተሊጀንስ ዩኒት (ኢ.አይ.ዩ) አካሄድኩት ባለው ዳሰሳ መሰረት ያወጣው መረጃ የሚያመላክተው፡፡
በአንጻሩ በጦርነት የወደመችው ሀገረ ሶርያ መዲና የሆነችው ዶማስቆ “በዓለማችን ኑሮ ቀላል የሆነባት” ከተማ ሆና ቀጥላለች፡፡ዳሰሳው የእቃዎች እና አገልግሎቶች ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት በ173 ከተሞች እንደተካሄደም ነው የተገለጸው፡፡
መረጃው በነሃሴ እና መስከረም ወራት እንደተሰበሰበ ያስታወቀው ኢ.አይ.ዩ ፤ ዋጋ ላይ በአማካይ የ3.5 በመቶ ጭማሪ መታየቱንና ይህም ካለፉት አምስት አመታት ወዲህ የታየ ከፍተኛ ጭማሪ ነው ብሏል፡፡
ዳሰሳ በተካሄደባቸው ከተሞች የትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ የተስተዋለ ሲሆን ፤ የቤንዚን ዋጋ ብቻ 21 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንም በአብነት ተነስቷል፡፡
ቴልአቪቭ በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ የእስራኤል ገንዘብ፤ ከዶላር አንጻር እያሽቆለቆለ ለመምፀጣቱ አመላካች መሆኑ ተገልጿል፡፡
ቴልአቪቭ አልኮልን በማጓጓዝ ከዓለማችን ሁለተኛ ስትሆን ፤ ለመዝናናት ወድ በመሆኗም በስድስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትቀመጥ የኢ.አይ.ዩ ዳሰሳ ያሳያል፡፡
የቴልአቪቭ ከተማ ከንቲባ ሮን ሁልዳይ ከ‘ሃረትዝ' ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ"ሀገሪቱ ውድ እየሆነች እንደምትሄድ ሁሉ፤ ቴልአቪቭ ከዚህ በላይ ውድ ትሆናለች" ሲሉ ተናግሯል፡፡
ከንቲባው አክለው "መሰረታዊው ችግር በእስራኤል ውስጥ ምንም አማራጭ የሜትሮፖሊታን ማእከል የለም፤ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ኒው ዮርክ, ቺካጎ, እና ማያሚ የመሳሰሉት አሉ፤ በብሪታንያ ውስጥ ታላቋ ለንደን, ማንቸስተር እና ሊቨርፑል አሉ፤ እዚያ ወደ ሌላ ከተማ መሄድ ይችላሉ.፤ እዚህ ግን የኑሮ ውድነቱ በጣም ከባድ ከሆነ" ብሏል፡፡
ኢኮኖሚስት ኢንተሊጀንስ ዩኒት (ኢ.አይ.ዩ) በባለፈው ዓመት ዳሰሳው ፓሪስ፣ዙሪክ እና ሆንግ ኮንግን፤ ለመኖር ከባድ የሆኑ የዓለማችን ከተሞች በሚል ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ማስቀመጡ አይዘነጋም፡፡
በዚህ ዓመት ግን ዙሪክ አራተኛ እንዲሁም ሆንግ ኮነግ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ኒውዮርክ፣ጀኔቫ፣ኮፐንሃገን፣ሎስአንጀለስ እና ኦሳካ በተርታ ተቀምጧል፡፡
የኢራኗ መዲና ቴህራን፤ ከ79ኛ ወደ 29ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ከፍ ያለች ሀገር መሆኗንም ነው ኢኮኖሚስት ኢንተሊጀንስ ዩኒት (ኢ.አይ.ዩ) አስታውቋል፡፡