የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ግብጽን እየጎበኙ ነው
የግብጽ አየር መንገድ ከመጪው ጥቅምት ጀምሮ ወደ እስራኤል የቀጥታ በረራዎችን ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል
ናፍታሊ ቤኔት ከፈረንጆቹ 2011 በኋላ ወደ ካይሮ ያቀኑ የመጀመሪያው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት በግብጽ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ናፍታሊ ከፈረንጆቹ 2011 በኋላ ወደ ካይሮ ያቀኑ የመጀመሪያው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡
ጉዞው ከባለፉት 10 ዓመታት ወዲህ በእስራኤል መሪ የተደረገ የመጀመሪያው የግብጽ ጉብኝት ነው፡፡
ቤኔት በጉብኝቱ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ እንዲሁም በፍልስጤም የሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጋር ይወያያሉ ተብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃገራቸው ሰንደቅ ዓላማ ባለበት ከፕሬዝንዳንት ሲሲ ጋር ሲወያዩ የሚያሳዩ ፎቶዎች መውጣታቸውም እስራኤላውያኑን እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ኔታንያሁ ከአሁን ቀደም ይህን ባለማድረጋቸው ሲወቀሱ ነበር፡፡
ግብጽ ለፍልስጤሟ ጋዛ መልሶ ግንባታ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር መመደቧን አስታወቀች
የግብጽ አየር መንገድ ከመጪው ጥቅምት ጀምሮ ወደ እስራኤል የቀጥታ በረራዎችን ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
ውሳኔው ከቤኔት ጉብኝት ጋር ይያያዝ አይያያዝ የታወቀ ነገር የለም እንደ እንደ ጀሩሳሌም ፖስት ዘገባ፡፡
ተሰናባቹ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ነበሩ በ2011 ወደ ካይሮ የተጓዙት፡፡ በዚያም ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክን አግኝተዋል፡፡
ናፍታሊ ቤኔት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሃላ ፈጸሙ
ይህ የሆነው ሙባረክ ከስልጣን ከመወገዳቸው ከአንድ ወር በፊት ነበር፡፡
ኔታንያሁን ተክተው የመሪነቱን ስልጣን የጨበጡት ናፍታሊ ቤኔት ግብጽን እንዲጎበኙ በአል ሲሲ ተጋብዘው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ቤኔት በቅርቡ ወደ አሜሪካ አቅንተው ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር መወያየታቸውም አይዘነጋም፡፡