ጣሊያናውያን በኑሮ ውድነት ሳቢያ ምግብ ለመቀነስ ተገደዋል ተባለ
ጣሊያናውያን ለምግብ ፍጆታ የሚያወጡት ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን ሪፖርት አመላክቷል
የጣሊያን የብሔራዊ የሸማቾች ህብረት ኃላፊ “ጣሊያኖች በዋጋ ንረት ምክንያት በግዳጅ ጾም ላይ ናቸው” ብለዋል
ጣሊያናውያን ከፍተኛ ከሆነ የዋጋ ንረት የተነሳ የምግብ ፍጆታቸውን ለመቀነስ መገደዳቸውን አዲስ የወጣ ሪፖርት አመላክቷል።
የጣሊያን ኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን (ኮንፊንዱስትሪያ) ባወጣው ሪፖርት መሰረት እየጨመረ ያለው የዋጋ ንረት ጣሊያናውያን ቤተሰቦች ለምግብ የሚያወጡትን ወጪ እንዲቀንሱ እያደረጋቸው ነው ብሏል።
ሪፖርቱ የጣሊያናውያን ቤተሰቦች የምግብ ፍጆታ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱን ያመላከተ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2022 አራተኛ ሩብ ዓመት ላይ ብቻ የምግብ ወጪ ዋጋ በ8.7 በመቶ መቀነሱ ተመላክቷል።
የጣሊያን ብሔራዊ የሸማቾች ህብረት (ዩኤንሲ) ኃላፊ ማሲሚሊያኖ ዶና ሪፖርቱን ጣሊያናውያን መዋግ ንብረት ሳቢያ ምግብ ለመቀነስ መገደዳቸውን “አሳዛኝ” ሲሉ ገልጸዋል።
ኃላፊ ማሲሚሊያኖ ዶና አክለውም፤ “ጣሊያኖች በከፍተኛ የዋጋ ንረት ምክንያት በግዳጅ ጾማ ላይ ናቸው” ሲሉም ሁኔታውን አብራተዋል።
የምግብ ፍጆታ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ውስጥ 60 በመቶውን ይሸፍናል ያሉት ኃላፊው፤ “ጣሊያናውያን ካልገዙ ነጋዴዎች መሸጥ አይችሉም፤ አምራቾችም ማምረተ ያቆማሉ፤ ሁኔታው በኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩን ጠቁመዋል።