ሙዝ የሚወዱት ጃፓናዊት ሴት የአለም በእድሜ ትልቋ ሴት ሆኑ
ኢቶካ የአለም ቁጥር አንድ የእድሜ ባለጸጋ መሆናቸው ሲነገራቸው "አመሰግናለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል
ቶሚካ ኢቶካ የተባሉት የ116 አመት ጃፓናዊት አዛውንት፣ የ117 አመቷ ማሪያ ብሪንስ መሞታቸውን ተከትሎ በህይወት ያሉ በእድሜ ትልቋ ሴት ሆነዋል
ሙዝ የሚወዱት ጃፓናዊት ሴት የአለም በእድሜ ትልቋ ሴት ሆኑ።
የጊኒየስ ወርደል ሪከርድ እንዳለው ቶሚካ ኢቶካ የተባሉት የ116 አመት ጃፓናዊት አዛውንት፣ የ117 አመቷ ማሪያ ብሪንስ መሞታቸውን ተከትሎ በህይወት ያሉ በእድሜ ትልቋ ሴት ሆነዋል።
በፈረንጆቹ ግንቦት 23,1908 መወለዳቸው ከመቶ አመት በላይ እድሜ ያላቸውን ሰዎች እድሜ በሚያመሳክረው ጄሮንቶሎጂ የጥናት ቡድን ተረጋግጦ፣ ሴትዮዋ ከ100 አመት በላይ እድሜ ካላቸው በህይወት ከሚኖሩ ሰዎች ውስጥ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ኢቶካ የልደት ቀናቸውን ባረጋጠጠው በአሽያ ከተማ በሚገኝ የእንክብካቤ ጣቢያ እንደሚገኙ ኤፒ ዘግቧል። ሴትየዋ የአለም በአድሜ ትልቋ የሚባለውን መጠሪያ ያገኙነት፣ የብራያንስ ቤተሰቦች የ117 አመት እድሜ ባለጸጋዋ መሞታቸውን ባለፈው ማክሰኞ ካሳወቁ በኋላ ነው።
ጊኒየስ ኢቶካ የአለም ባለትልቅ እድሜ ሴት መሆናቸውን አረጋግጧል።
ኢቶካ የአለም ቁጥር አንድ የእድሜ ባለጸጋ መሆናቸው ሲነገራቸው "አመሰግናለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ኢቶካ የልደት ባዓላቸው ከሶሰት ወራት በፊት ሲያከብሩ አበባ፣ ኬክ እና የልደት ካርድ ከከንቲባው ተበርክቶላቸው ነበር። ሴትዮ የሚወዱት ምግብ ሙዝ ነው።
በኦሳካ የተወለዱት ኢቶካ በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳሉ የእጅ ኳስ ተጨዋች ነበሩ።ጊኒየስ እንደገለጸው ኢቶካ በ20 አመታቸው ያገቡ ሲሆን ሁለት ሴቶች እና ሁለት ወንጆች ልጆች አሏቸው።
ኢትዮካ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት የባለቤታቸውን የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ይቆጣጠሩ ነበር። ባለቤታቸው በ1979 የሞተባቸው ኢቶካ በናራ ብቻቸውን ይኖሩ ነበር።