ጀኒፈር ሎፔዝ ለአራተኛ ጊዜ ትዳሯን ለመፍታት ክስ መሰረተች
ጥንዶቹ ከዚህ በፊት በይፋ የተፋቱ ቢሆንም ድጋሚ ታርቀው ተጋብተው ነበር
ዝነኛዋ ድምጻዊ እና የሆሊውድ ተዋናይ ጀኒፈር ከቤን አፍሌክ ጋር ፍቺ ጠይቃለች
ጀኒፈር ሎፔዝ ለአራተኛ ጊዜ ትዳሯን ለመፍታት ክስ መሰረተች፡፡
ጄሎ በሚል ስሟ የምትታወቀው የ55 ዓመቷ አሜሪካዊት የኪነ ጥበብ ሙያተኛ ጀኒፈር ሎፔዝ ከሙያ አጋሯ ቤን አፍሌክ ጋር ያላት ጋብቻ እንዲፈርስ የፍቺ ጥያቄ ለፍርድ ቤት አቅርባለች ተብሏል፡፡
ጄሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ትዳር የመሰረተችው በፈረንጆቹ 1997 ላይ የዘር ሀረጉ ከኩባ ከሚመዘዘው ኦጃኒ ኖአ ጋር ነበር፡፡
ከአንድ ዓመት በላይ ያልዘለቀው ይህ ትዳር በፍቺ ከተጠናቀቀ በኋላ ከዳሰኛው ጁድ ክሪስ ጋር ሁለተኛ ትዳሯን በ2001 ላይ ፈጽማለች፡፡
ይህ ትዳር ከሶስት ዓመት በኋላ መፍረሱን ተከትሎ ከድምጻዊ ማርክ አንቶኒ ጋር በትዳር የተጣመረች ሲሆን ረጅም ጊዜ የቆየ ትዳሯ ሆኗል፡፡
ከድጻዊ አንቶኒም መንታ ልጆችን ከወለደች በኋላ ይህ ትዳሯ እስከ 2014 ድረስ መዝለቅ ከቻለ በኋላ የኒዮርክ ነዋሪው የፊልም ባለሙያ አሌክስ ሮድርጊውዝ ጋር ቀለበት አስራም ነበር፡፡
የትዳር ፍቺ የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት የትኛቹ ናቸው?
ጄሎ የፍቺ ጥያቄ ካቀረበችለት ቤን አፍሌክ ጋር በፈረንጆቹ 2003 ላይ የፍቅር ግንኙነት ከጀመሩ ከአንድ ዓመት በኋላ የመጋባት እቅድ የነበራቸው ቢሆንም ፍቅራቸው ሳይቀጥል ቀርቷል፡፡
ሁለቱም ዝነኛ ተዋዮች ከብዙ ዓመታት በኋላ በድጋሚ ፍቅር ጀምረው በ2022 በይፋ የተጋቡ ቢሆንም ከሁለት ዓመት በኋላ ድጋሚ የፍቺ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡
ጥንዶቹ በጋራ ሲኖሩበት የነበረው ቅንጡ መኖሪያ ቤት በ65 ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ ማስታወቂያ ያወጡ ሲሆን የትዳር ቀለበታቸውም በጣቶቻቸው ላይ እንደሌለ አስቀድመው ሚዲያዎች ዘግበው ነበር፡፡
ቤን አፍሌክ የአሁን ትዳሩ ሁለተኛው ሲሆን ሶስት ልጆችን ካፈራበት ከጀኒፈር ጋርነር ጋር የነበረው ትዳር በ2015 በፍቺ ተጠናቋል፡፡