ጃፓን በሰሜን ኮሪያ የሳተላይት ስጋት የሚሳይል ጥበቃ ማስጠንቀቂያ አወጣች
ሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያውን ወታደራዊ ሰላይ ሳተላይት ለማምጠቅ የመጨረሻ ዝግጅት ላይ መሆኗን አስታውቃለች
ቶኪዮ በግዛቷ ይወድቃሉ ተብለው በተረጋገጡ ሚሳይሎች ላይ አጥፊ እርምጃዎችን እንወስዳለሁ ብላለች
ጃፓን ሰኞ እለት የባሊስቲክ ሚሳይል መከላከያዋን በተጠንቀቅ ላይ አድርጋ ግዛቷን የሚያሰጋ ማንኛውንም ቁስ እንደምትመታ አስጠንቅቃለች።
ይህ የሆነው ሰሜን ኮሪያ ከግንቦት 31 እስከ ሰኔ 11 ባለው ጊዜ ውስጥ ሳተላይት እንደምታመጥቅ ለጃፓን ካሳወቀች በኋላ ነው።
ሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያውን ወታደራዊ ሰላይ ሳተላይት እንዳጠናቀቀች ገልጻ፤ መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን ለማምጠቅ የመጨረሻ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን አሳውቀዋል።
ተንታኞች ሳተላይቱ በጦርነት ጊዜ ኢላማዎችን የመምታት አቅሟን ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ያካተተ የስለላ ቴክኖሎጂ ፕሮግራም አካል ነው ብለዋል።
የጃፓን መከላከያ ሚንስቴር በሰጠው መግለጫ "በክልላችን ውስጥ ይወድቃሉ ተብለው በተረጋገጡ ባሊስቲክ እና ሌሎች ሚሳይሎች ላይ አጥፊ እርምጃዎችን እንወስዳለን" ብሏል።
ሚንስቴሩ የሰሜን ኮሪያን ሚሳኤል ለማጥፋት "ስታንዳርድ ሚሳይል-3" ወይም "ፓትሪዮት ሚሳይል" እንደሚጠቀም ገልጿል።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ማንኛውም የሰሜን ኮሪያ ሚሳይል ማስወንጨፍ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም/ቤት የኒውክሌርና የሚሳይል እንቅስቃሴን የሚጥስ ነው ብለዋል።
የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤቱ በትዊተር ገፁ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ሰሜን ኮሪያን ከእንቅስቃሴዋ እንድትታቀብ "አጥብቀን እናሳስባለን" ብሏል።
አጋር ሀገራት አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ሌሎች ሀገራት ጋር ትብብር እንደሚኖርም ገልጿል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ደቡብ ኮሪያም ከጃፓን ጋር በመሆን ሰሜን ኮሪያ ልታመጥቅ ያቀደሰውን ሳተላይት እንድትሰርዝ ጠይቃለች።