ጃፓን የሚያገቡ ዜጎቿን ለማበረታታት የመጠባበሻ መተግበሪያ ሰራች
በጃፓን በየዓመቱ ከሚወለዱ ህጻናት ይልቅ የሚሞቱት በእጥፍ ይበልጣሉ
የህዝብ ቁጥሯ ማሽቆልቆል ያሳሰባት ጃፓን በመንግስት ወጪ አጋር መፈለጊያ መተግበሪያ ሰርታለች
ጃፓን የሚያገቡ ዜጎችን ለማበረታታት የመጠባበሻ መተግበሪያ ሰራች፡፡
በአዛውንቶች ህዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነችው ጃፓን የሚወለዱ ህጻናት ቁጥርን ለመጨመር በሚል የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመዘርጋት ላይ ትገኛለች፡፡
የጃፓን መዲና እና ከ22 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት ቶኪዮ ደግሞ የውልደት መጠን ዝቅተኛ ነው፡፡
የከተማዋ አስተዳድር ይህን ለመፍታት በሚል ዜጎች እንዲጋቡ እና ልጆችን እንዲወልዱ በሚል አጋራቸውን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ መተግበሪያ ሰርቷል፡፡
ይህን አፕሊኬሽን ወይም መጠባበሻ መተግበሪያ ለመጠቀም ገቢ ያለው መሆን፣ ያላገባ ማስረጃ መኖር፣ ግብር መክፈሉን እና ማንነቱን የሚያሳዩ መረጃዎችን ማቅረብ እንደ ግዴታ አስቀምጧል፡፡
ይሁንና ይህን የአጋር መፈለጊያ መተግበሪያ እንዲጠቀሙ ከሚጠበቁ ጃፓናዊያን መካከል 70 በመቶዎቹ ፍላጎት አላሳዩም ሲል ኤአፍፒ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ጃፓናዊን በመንግስታቸው ውሳኔ ተገርመዋል የተባለ ሲሆን አንዳንዶቹ ግብር የምንከፍለው ለእንደዚህ አይነት ስራ አልነበረም እያሉ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ሀሳባቸውን እያጋሩ ይገኛሉ፡፡
ጃፓን የምግብን ጣዕም በራሱ ጊዜ የሚመጥን ዘመናዊ ማንኪያ ሰራች
ገሚሶቹ ደግሞ የአጋር መፈለጊያ መተግበሪያው መዘጋጀቱ ትዳር መያዝ እና ልጅ የመውለድ ፍላጎቱ ላላቸው ዜጎች ጥሩ አማራጭ እንደሚሆንላቸው ጽፈዋል፡፡
በጃፓን በየዓመቱ ከሚወለዱ ህጻናት ይልቅ የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ሲሆን በዚህ ምክንያት ከፍተኛ የሰራተኞች እጥረት እያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡
ባሳለፍነው ዓመት ብቻ በጃፓን የተወለዱ ህጻናት ቁጥር 759 ሺህ ብቻ ሲሆን የሞቱ ጃፓናዊያን ቁጥር ግን 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ነበር፡፡