ጃፓን ውስጥ ተሰራችው በአለም የመጀመሪያዋ የእንጨት ሳተላይት ወደ ጠፈር ተወነጨፈች
በኪዮቶ ዩኒቨርስቲ እና በሱሚቶሞ ፎረስትሪ በጋራ የተሰራችው ሊግኖሳት ከመሬት በላይ እስከ 400 ኪሎሜትር ባለው ርቀት ምህዋር እንደምትለቀቅ ተገልጿል
የእጅ መዳፍ ያህል መጠን ያላት ሊንጎሳት ታዳሽ ቁሶች በጠፈር ላይ ጥቅም እንደሚሰጡ ለማሳየት ታስቦ የተላከች ነች ተብሏል
ጃፓን ውስጥ ተሰራችው በአለም የመጀመሪያዋ የእንጨት ሳተላይት ወደ ጠፈር ተወነጨፈች።
በጃፓን ሳይንቲስቶች የተሰራችው በአለም የመጀመሪያ የእንጨት ሳተላይት ባለፈው ማክሰኞ ወደ ጠፈር መወንጨፏን ሮይተርስ ዘግቧል።
በኪዮቶ ዩኒቨርስቲ እና በሱሚቶሞ ፎረስትሪ በጋራ የተሰራችው ሊግኖሳት በስፔስ ኤክስ ሚሽን ወደ አለምአቀፍ ስፔስ ስቴሽን እንደምትጓዝ እና ቆይታም ከመሬት በላይ እስከ 400 ኪሎሜትር ባለው ርቀት ምህዋር እንደምትለቀቅ ተገልጿል።
በላቲን ቃል "ውድ" ተብላ የተሰየመችው የእጅ መዳፍ ያህል መጠን ያላት ሊንጎሳት የሰው ልጅ በጠፈር መኖር ስለሚፈልግ ታዳሽ ቁሶች በጠፈር ላይ ጥቅም እንደሚሰጡ ለማሳየት ታስቦ የተላከች ነች።
"እኛ ባመረትነው ጣውላ፣ ጠፈር ውስጥ ቤት መገምባት፣ መኖር እና መስራት እንችላለን" ሲል በጠፈር መንኮራኩሯ የበረሩት እና በክዮቶ ዩኒቨርሲቲ የሰው ልጅን የጠፈር እንቅስቃሴ የሚያጠኑት ታካኦ ዶይ ተናግረዋል።
በ50 አመት ውስጥ ጨረቃ እና ማርስ ላይ ዛፍ ለመትከል እና የጣውላ ቤት ለመገንባት አቅደው እየሰሩ ያሉት የዶይ ቡድን እንጨት ለጠፈር ተስማሚ መሆኑን ለማረጋገጥ በናሳ እውቅና ያገኘ ሳተላይት ሰርተዋል።
የክዮቶ ዩኒቨርሲቲ የፎሬትስት ሳይንስ ፕሮፌሰር ኮጂ ሙራታ እንዳሉት "በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ አውሮፕላኖች የሚሰሩት በእንጨት ነበር።" "የእንጨት ሳተላይትም መሳካት አለበት።"
ፕሮፌሰሩ አክለውም እንጨት ከመሬት ይልቅ ጠፈር ላይ የተሻለ እድሜ ይኖረዋል፤ ምክንያቱም ሊያበሰብሰው ወይም ሊያነደው የሚችል ኦክስጅን እና ውሃ የለም ይላሉ።
ዶይ እንደገለጹት የተለመዱት የብረት ሳተላይቶች ወደመሬት በሚመለሱበት ጊዜ አሉምኒየም ኦክሳይድ ይፈጥራሉ፤ የእንጨቶቹ ግን በዝቅተኛ የብክለት መጠን ይቃጠላሉ።
"ወደፊት የብረት ሳተላይቶች ከገበያ ሊታገዱ ይችላሉ" ብለዋል ዶይ። "የመጀመሪያችን የሆነው የእንጨት ሳተላይት ከሰራ፣ ለኢለን መስኮ ስፔስ ኤክስ እናቀርባለን።"