ሩሲያ በመሬት ላይ ያለውን ከባቢያዊ የአየር ሁኔታ የሚቆጣጠሩ ሁለት ሳተላይቶቸን ጨምሮ 53 ሳይተላይቶችን ማምጠቋን የሩሲያው ሮስኮስሞስ ስፔስ ኤጀንሲ አስታውቋል
ሩሲያ በሶይዙ ሮኬት በደርዘን የሚቆጠሩ ሳይተላይቶችን አመጠቀች።
ሩሲያ በመሬት ላይ ያለውን ከባቢያዊ የአየር ሁኔታ የሚቆጣጠሩ ሁለት ሳተላይቶቸን እና ከኢራን የመጡ ሁለት ሳይተላይቶችን ጨምሮ 53 ሳይተላይቶችን የተሸከመ ሶይዙ ሮኬት በዛሬው እለት ማምጠቋን የሩሲያው ሮስኮስሞስ ስፔስ ኤጀንሲ አስታውቋል።
ኤጀንሲው እንደገለጸው ከሩሲያ ቮስቶቺኒ ኮስሞድሮም የተነሳው ሶይዙ2.1 ሮኬት የመሬትን አዮኖስፌር ክፍል ለመከታል የሚያስፈልጉ ሎኖስፌራ-ኤም ሳተላይቶችን ወደ ህዋ አምጥቋል። አንደ አሜሪካው የጠፈር ምርምር ማዕከል ናሳ ከሆነ የመሬት ከባቢ አየር ከህዋ ጋር የሚገናኝበት አዮኖስፌር ከመሬት ገጽ በላይ ከ80 እስከ 644 ኪሎሜትር ርቀት ይሸፍናል።
የእያንዳንዱ ሎኖስፌራ-ኤም ክብደት 430 ኪሎግራም ሲሆን የሚሰራበት ምህዋር ወይም ኦርቢት 820 ኪሎሜትር መሆኑን ሮይተርስ የሩሰያውን ኢንተርፋክስ ዜና አገልግሎት ጠቅሶ ዘግቧል።
ሲተስተሙ አራት ሎኖስፌራ-ኤም ሳተላይቶችን ያካተተ ነው። ሮስኮስሞስ እንደገለጸው ቀጣዮቹ ሁለት መሳሪያዎች በ2025 ይላካሉ።
ከ53 አነስተኛ ሳተላይቶች ውስጥ የኢራኖቹ ከፍተኛ የምስል ጥራት ያለው ኮውሳር እና አነስተኛ የኮሙኒኬሽን ሳይተላይት ሆድሆድ እንዲሁም የመጀመሪያው የሩሲያ-ቻይና ተማሪዎች ሳተላይት ዱርዝህባ አቱርክ ሳተላይት ይገኙበታል።
ሩሲያ ባለፈው የካቲት ወር የኢራንን መልካምድር የሚያስስ ሳተላይት ወደ ህዋ ማምጠቋን በወቅቱ ተዘግቦ ነበር።